እኔ ክርስትያን ነኝ ብላ ዳኛውን ያስቆጣችው መርያም ከሙስሊም ሱዳናዊ እና ከክርስትያን ኢትዮጵያዊ የተወለደች ሲሆን ወላጅ አባቷ ሲለይ በክርስትያን እናቷ የክርስትናን ሃይማኖት እየተከተለች ያደገች ነበረች :: መርያም በፕሊስ ቁጥጥር በዋለችበት ወቅት የ8 ወር ነፍሰ ጡርም ነበረች :: ባለቤቷ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በመሆኑ እርግዝናዋ ከትዳር ውጭ በማለት (አንድ ሰው ባባቱ ሙስሊም ከሆነ የ እስልማና ሃይማኖት ተከታይ ነው የሚሆነው ይህ ደግሞ የሱዳን መንግስት የሽርያ ህግ ነው) ፍርድ ቤቱ ጋብቻዋን ውድቅ በማድረግ 100 ጅራፍ እንድትገረፍና ዳኛ ፊት ቀርባ ክርስትያን ነኝ ብላ በመከራከሯ ደግሞ በድንጋይ ተቀትቅጣ እንድትሞት የተፈረደባት መሆኑንም ተዘግቦ ነበር ::
አንድ ሚልየን የሚየን የሚጠጋ የፊርማ የተሰበሰበላት መርያም ዛሬ በነፃ ተለቃ ባለቤቷንና ልጆችዋን ተቀላቅላለች :: የአለም ሕዝብን ልብ የሰረቀችው መርያም ለቤቷ ያበቃት እግዚያብሔርም ምስጋና ይግባው ::
አሜን !!
አሜን !!
ሁሌም መልካም ስሩ !!
No comments:
Post a Comment