Wednesday, February 5, 2014

(ሰበር ዜና) በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ዙሪያ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

debereselam Minnesota
(Updated) (ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ውስጥ የተፈጠረውን የሃሳብ ልዩነትና የህግ ተጥሷል ጥያቄ በተመለከተ በገለልተኛነት እንዲቆይ ከሚፈልገው ወገን በተወከሉት ወገኖች የቀረበውን አቤቱታ እና በተከላካይ ደብረሰላም ቦርድ መካከል ያለውን ጉዳይ (Temporary Restraining Order Hearing) የተመለከተው የሚኒሶታው ፍርድ ቤት ዛሬ ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አባላት ተሰብስቦ የቤተክርስቲያኒቱን ቀጣይ ሁኔታ እንዲወስን ያ ካልሆነ ለማርች 10 ቀን 2014 ክሱ መታየት እንዲቀጥል ውሳኔ አስተላለፈ።
በፍርድ ቤቱ ከታደሙ እማኞች ባገኘነው መረጃ መሠረት የሚኒሶታ ስቴት የሄኒፐንካውንቲ ፍርድ ቤት (state of Minnesota, county of Hennepin district court fourth judicial district) በሁለቱም ወገኖች በጠበቆች አማካኝነት የቀረበውን አቤቱታ ከተመለከተ በኋላ የቤተክርስቲያኑን ቀጣይ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ምዕመናኑ እንዲወስን፤ ያካልሆነ ግን ለማርች 10 ቀን 2014 ቀጣይ ቀጥሮ እንዲሆን አዟል። በዚህም መሠረት እሁድ ፌብሩዋሪ 23 ቀን 2014 በደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ አባላት ተሰብስበው የቤተክርስቲያኒቱን አጠቃላይ ሁኔታ ለመወሰን ቀጠሮ ተይዟል።

“ቤተክርስቲያኑ ወደ ሃገር ቤት ሲኖዶስ እንዲቀላቀል የሚፈልገው” ወገን በጠበቃው አማካኝነት የቀድሞውን ሊቀመንበርን በሚመለከት ቀድሞ ያሰባሰበውን ፒትሽን በጠበቃው አማካኝነት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በቦርዱ አዲስ የተሾመውንም ሆነ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሊቀመንበር ሳይቀበል ቀርቷል። በሌላ በኩል “በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ያለው ሲኖዶስ መካከል እርቀሰላም እስኪወርድ ድረስ በገለልተኛነት መቆየት አለብን” የሚለው ወገን ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራልን በሚል ያሰባሰበውን የምዕመናን ፒትሽን በጠበቃው አማካኝነት ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ሲታወቅ፤ የፍርድ ቤቱ ዳኛ ቹ ሬጂና ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ እንዲወሰን አዘዋል።
አሁን በደረሰን መረጃ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የማይወሰን ከሆነ ፍርድ ቤቱ በማርች 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጉዳዩ ይታያል።
(ተጨማሪ መረጃዎች ከደረሱን አሁንም ዜናውን በአዳዲስ መረጃዎች እናድሰዋለን።)
Source: Zehabesha

No comments:

Post a Comment