Friday, February 7, 2014
ሰበር ዜና በሪያድ የኢትዮጵ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራ ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ እመራር ኮሚቴ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በታደሙ አባልት እና የአንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ በሚታወቁት የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ደጋፊዎች መሃከል ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ወደ ግጨት አምርቶ እንደነበር ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል።
የስብሰባውን ታዳሚ ግራ ያጋባው ይህ ግጨት መነሻው የቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሼክ ሙሰጠፋ ሁሴን ለምን ከስልጣኔ ተነሳሁ በሚል በምከትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ላይ ቡጢ መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሼክ ሙስጠፋ ከስብሰባው በፊት ሲያስተባብሯቸው የነበሩ ከ 50 የሚበልጡ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት ሁከት የመስብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ፡ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ማምሸቱን ጠቅሰዋል። ....
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ በአካቢው የተፈጠረውን አለመረጋጋት የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባውን ለሌላ ቀን ለማስተላለፍ መገደዱን የሚገልጹት ምንጮች የሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች ጩቤ ታጠቀው ወደ አዳራሹ ገብተው እንደነበር ቢገልጹም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ ውስጥ ዛሬ በተነሳው አንባጓሮ የተጓዳ ሰው እደሌለ አረጋግጠዋል ። ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ቀደም ሲል በሪያ የኢትዮጵያ ኮሚቲ ለቀመንበር እንደንበሩ እና ምንጩ በግልጽ የማይታወቅ ሁለት ሚልዮን ሪያል በግል ካዝናቸው ተገኝቶ በሳውዲ መንግስት የደህነንት ሃይሎች ታስረው መክረማቸውን ተከትሎ የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በማህበሩ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መስረት የስልጣን ሽግሸግ ለማድረግ በመገደዱ ግለስቡን ከሃላፊነታቸው ማስወገዱን ይናገራል። ዛሬ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ ተከስተ በተባለው ሁከት በሳውዲ የኢትዮጵያው አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን እጅ እንዳለበት የሚገልጹ ወገኖች ሃገር እና ህዝብን ወክሎ ከተቀመጠ አንባሳደር የሚጠበቅ እንዳልሆነ በማውሳት ድርጊቱን አውግዘዋል።
ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ የአንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ዝምድናን መከታ በማድረግ በኤንባሲው ማህተም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጀቶች ገንዘብ በመሰብሰብ ከአንባሳደሩ ጋር ለግልጥቅማቸው ሲያውሉ የነበሩ መሆናቸውን የሚያወጉ የሪያድ ነዋሪዎች ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ኢትዮጵያ ውስጥ በከፈቷቸው 2 ኤጀንሲዎቻቸው በመታገዝ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እስከ 7 መቶ ዶላር በመሰብሰብ በእህቶቻችን ህይወት ሲነግዱ የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ በህገወጥ የሃላ ንግድ ተሰማርተው ከቀርብ ግዜ ወዲህ የከበሩ ሃብታም ነጋዴ እና የአንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ባለው ለታ መሆናቸው ይናገራል ።
ዛሬ ተቀሰቀሰ በተባለው ግጨት ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ የዲያስፖራውን ሃልፊ ለማንገጋር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ።
በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን ከወኒ መወጣት እና እጃቸው ላይ ተይዞ ስለነበረው 2 ሚልዮን ሪያል « 10 ሚልዮን ብር » የድረሱንን መረጃዎች ወድፊት አጠናቅረን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፤
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment