የኢትዮጵያ ቡድናዊ አምባገነኖች ለአልበሽር አዎንታዊ መልስ የሰጡ ሲሆን የእርትራ ችግር የአለማኣቀፍ እና የምስራቅ አፍሪካ ችግር ስለሆነ መጀመሪያ ይህንን የቤት ስራዋን ትጨርስ ብለዋል::
"ኢሳያስ እያጭበረበረ ነው::" ኤርትራውያን ምንጮች
ከምስራቅ አፍሪካ አምባገነን መሪዎች አንዱ የሆኑት የሱዳኑ መሪ ኦመር አልበሽር የኤርትራው መሪ ብቸኛ እና የቅርብ ወዳጅ መሆናቸው ይታወቃል:: ይህንኑ መሰረታቸውን ይዘው የኳታርን ሽርክና አዳብለው ወደ አስመራ ከአጋር አምባገነን ባለስልጣኖቻቸው ጋር አስመራ የሚመላለሱት የሱዳኑ መሪ በወያኔ እና በሻእቢያ መካከል የተነሳውን አለመግባባት ለመፍታት ባደረጉት ጥረት የኤርትራው አምባገነን መሪ ከኢትዮጵያ ቡድናዊ አምባገነን መሪዎች ጋር እርቀ ሰላም ለማውረድ ፈቃደኝነታቸውን መግለጻቸው የሱዳን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ጠቁመዋል::
ኢሳያስ አፈወርቂ ከሁለት ወር በፊት በካርቱም ያደረጉት ጉብኝት የኳታር አሚሮች በአስመራ ያደረጉት ጉብኝት የሕወሓት አሻንጉሊት ሃይለማርያም በኳታር ያደረገው ጉብኝንት እና ሌሎች ዲፕሎማሲያዊ ሂደቶችን ተከቶ በቅርቡ የሱዳኑ መሪ በአስመራ ያደረጉትን ጉብኝት ደምሮ በተደረገው ጥረት እንዲሁም አይቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳኑ መሪ ላይ ግንኙነቱ እንዲሻሻል እንዲሰሩ ባደረጉት ግፊት የተፈጸመው ይህ ፕሮፖዛል ወደ መጠናቀቅ መቃረቡን ምንጮቹ ተናግረዋል::
የሱዳን ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳሉት አይቶ ኢሳያስ አፍወርቂ በአስቸኳይ ድርድሩ እንዲጀመር እና እርቀሰላሙ እንዲፈጸም ከፍቃደኝነታቸው ጨምሮ ግፊት እያደረጉ ነው:: አቶ ኢሳያስ ለአልበሽር እርቀሰላሙ እንዲፋጠን በጠየቁት መሰረት በጃንዋሪ 29 2014 አዲስ አበባ ላይ ለሃይለማርያም ደሳለኝ የፕሮፖዛሉን ሁኔታ እና የአቶ ኢሳያስ ስምምነትን በኔፓድ ስብሰባ ወቅት እንዳስረዷቸው ታውቋል::ይህንን የሰሙት የኢትዮጵያ ቡድናዊ አምባገነኖች ለአልበሽር አዎንታዊ መልስ የሰጡ ሲሆን የእርትራ ችግር የአለማኣቀፍ እና የምስራቅ አፍሪካ ችግር ስለሆነ መጀመሪያ ይህንን የቤት ስራዋን ትጨርስ ብለዋል::
ካሁን በኋላ የእርትራን ምድር እና ሕዝብ መውረር አንፈልግም ያሉት የኢትዮጵያ ቡድናዊ አምባገነን መሪዎች ኢሳያስን ዳህላክ ላይ እንደሚገድቧቸው ተናግረዋል:: አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ግን ይህ የእርቀሰላም ስምምነት ኢሳያስ በሃሰት ያቀረበው እና ግርማ አስመሮም ወደ አዲስ አበባ እንዲመላለስ እና ስብሰባዎችን እየተካፈለ የስለላ መረጃዎችን እንዲሰበስብ የተደረገ የማጭበርበሪያ ስልት ነው እንጂ ሌላ ምንም ምስጢር የለውም ብለዋል::
via:EthiopianReview#BY ምንሊክ ሳልሳዊ#
No comments:
Post a Comment