Wednesday, February 5, 2014

ስንቶቻችን ስልካችንን እናምነዋለን? የገዛ ስልካችን አሳልፎ ሲሰጠን!!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሞባይል ስልክ ግንኙነት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ይገኛል። የጥራቱ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ቢገኝም ኢትዮ ቴሌኮም ከ17 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን እያገናኘሁ ነው ብሎናል።
ኢትዮጵያ ከሌሎች አፍሪካ አገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ዝቅተኛ የሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ ስርጭት እንዳላት መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በኢትዮጵያ መንግስት ካለምንም ተቀኛቃኝ በቁጥጥር ስር የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞችን በኔትወርክ እጦት ቢያማርርም ትኩረት ያልተሰጠው ትልቁ አደጋ ግን በመንግስት የደህንነት ሀይሎች የሚደረግ የስልክ ጠለፋና ስለላ በተቋም ደረጃ ዋነኛ ተባባሪ መሆኑ ነው።
የሁለት ሰዎችን ግንኙነት ሚስጥራዊ ለማድረግ የስልክ ግንኙነትን ማስወገድ ዋነኛ መፍትሄ ነው። ተንቀሳቃሽ ስልኮች ሲፈጠሩ ጀምሮ መልእክት እንዲያስተላልፉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። ይህ መልእክት የማስተላለፍ ስራ ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው ወገን በሚደረግ የስልክ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን አንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ የያዘ ግለሰብ ስልኩን ቢጠቀምበትም ባይተቀምበትም የት አካባቢ እንዳለ የሚጠቁም መረጃ ወደ ሰርቪስ ፕሮቫይደሩ ይልካል።
ስለዚህ በሞባይል ስልክ የሚደረግ የመልእክት ልውውጥ ብቻ ሳይሆን ያ ግለሰብ የት የት ቦታ እየተንቀሳቀስን እንደሆነ የገዛ ሞባይላችን በስላላ ላይ ለተሰማራው አካል ሹክ ይለዋል ማለት ነው። አሁን አሁን በዘመናዊ መልክ እየተሰሩ ያሉ ስልኮች የሰውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ እያቀለጠፉ ቢሆንም ከደህንነት ጋር በተያያዘ አደጋቸው ግን የትየለሌ ነው።
ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ አፕሊኬሽኖች በግለሰብ ደረጃ እየተሰሩ ለአገልግሎት እንዲውሉ ቢደረግም፤ ዋነኛ ስራቸው ስለላ የሆነ ሶፍትዌሮችም ዲዛይን ተደርገው በየተንቀሳቃሽ ስልኮች ያለውን መረጃ ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍ እንዲመች ተደርገው አገልግሎት እየሰጡ ነው።
አንድ የስላላ ሶፍትዌር የተጫነበት ተንቀሳቃሽ ስልክ የዛን ስልክ ተጠቃሚ ግለሰብ ኢ-ሜይል፣ ኮንታክቶች፣ ምስሎች፣ እንዲሁም በስልኩ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ዶክምንቶች ወደ ሶስተኛ ወገን በመላክ የግለሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል።
ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን በሶስተኛ ወገን መጠለፋቸውን ለማወቅ ከስር የተጠቀሱትን ነጥቦች ልብ ማለት ይገባል።
★ ስልካችን የሚያሳየው ያልተለመደ ፀባይ፡-
  ስልኮች ከጊዜ ጊዜ የተለያየ ፀባይ ያመጣሉ ለምሳሌ፡ ሳንጠቀምበት ስልካቸን በመሃል የሚበራ ከሆነ፣ ያልተለመደ የ ቢፕ ድምፅ የሚያሰማ ከሆነ፣ በራሱ ሰአት የሚጠፋ ከሆነ ስልካችን ለስላላ ተግባር ዲዛይን በተደረጉ ሶፍትዌሮች አክሰስ እየተደረገ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው።
★የባትሪ ቶሎ ማለቅ፡- 
ብዛት ያላቸው አፕሊኬሽኖች የስልክን ባትሪ ይጨርሳሉ። የስለላ ሶፍትዌሮች የሚጠቀሙት የባትሪ ሀይል ከፍተኛ ነው። የስልክ ባትሪያችን ቶሎ ቶሎ የሚያለቅና ቻርጅ አርጉኝ የሚል ከሆነ ስላካችን ለስለላ ተግባር ዲዛይን በተደረገ ሶፍትዌር መጠቃቱ እንደ አንድ ምልክት ሊወሰድ ይችላል።
★ከበስተጀርባ የሚመጣ ድምፅ፡-
አብዛኘን ጊዜ መጥፎ የኔትወርክ ሽፋን ያለት አካባቢ የሚደረግ የስልክ ግንኙነት ከበስተጀርባ መሚመጣ ሰቅጣጭ ድምፅ የተጀበ ነው።
ኢትዮጵያ ካላት ደካማ የኔትወርክ ሽፈን አንፃር ከበስተ ጀርባ የሚመጡ ድምፆች የተለመዱ ስለሆነ ስልካችን እየተጠለፈ መሆኑን ለማወቅ ይከብዳል።
★ያልተለመዱ የፅሁፍ መልእክት፡-
የተለያዩ ቁጥሮች፣ የማይገቡ ካራክተሮች ወደ ስልካችን የሚላኩ ከሆነ በስልካችን ላይ የተጫነውን የስለላ ሶፍትዌር የሚቆጣጠረው ተቋም ወይም ግለሰብ የሚልኳቸው ሚስጥራዊ ኮዶች ናቸው።
የተላኩት ሚስጢራዊ ኮዶች ስልካችን ላይ የሚታዩት የስለላ ሶፍትዌሮች በሚገባ እየሰሩ ሳይሆን ሲቀር ነው። ይህም ስልካችን በስለላ ሶፍትዌር ተጠቅጦ እንደነበር በቂ ማሳያ ሊሆን ያችላል።
★ስልካችን ላየ ያለው የዳታ መጠን ሲጨምር፡- 
ስልካችን ላይ ያለው የዳታ መጠን ሲጨምር ወይም ስልካችን ዳታ የመያዝ አቅሙ እያነሰ ሲመጣ ከኛ እውቅና ውጪ የሆነ ዳታ ስልካችን ላይ እንዳለ እንገነዘባለን፤ ለዚህም አንዱ ምክንያት በስልካችን ላይ የሚገኘው የስለላ ሶፍትዌር ስልካችን ላይ የሚገኙትን መረጃዎች ወደ ሶስተኛ ወገን ለመላክ በሚያዘጋጅበት ጊዜ የራሱን የሚሞሪ ስፔስ ስለሚጠቀም ነው።
★ጠፍቶ የነበረ ስልክ ድንገት ሲበራ፡- 
በሰላም አገር ስልካችንን አጥፍተን በተቀመትንበት ማንም ሳይነካው ሊበራ ይችላል። ሰርቪስ ፕሮቫይደሩ በገዛ ስልካችን የጠፋ ስልካችንን አብርቶ አሁንም በገዛ ስልካችን ሊደውልልን ይችላል። የዚን ያህል ስልካችን ደህንነቱ አደጋ ላይ የወደቀ ነው።
ከላይ የተጠቀሱት ለደህንነት ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ምልክቶች ወደፊት የሚኖረንን የስልክ ግንኙነት በጥንቃቄ የተሞላ እንዲሆን ይረዱናል። ከዚህ ባሻገር እንደመፍትሄ ሊወሰድ የሚችለው ነገር ምንም አይነት ግለሰብን አደጋ ላይ የሚጥሉ መረጃዎች ወይም ሚስጥራዊ ውይይቶች የስልክ ግንኙነቶችንና የስልክ ቀፎዎችን ያራቁ መሆን ይኖርባቸዋል።
አንድ ግለሰብ ብቻውን ቢሆን እንኳን የሚያወራው ሚስጥር አጠገቡ የስልክ ቀፎ ካለ {የጠፋ ቢሆን እንኳ} ሚስጥርነቱ አጠራጣሪ  ይሆናል!!!
http://secamharic.blogspot.com/2014/02/blog-post_4.html?spref=tw

2 comments:

  1. The best way of stopping phone tapping and hacking is exposing the hackers on social media to the world, as did Egyptian in the 2011 Arab Spring revolution. Above all, dictatorial regime can't control thousands of telephone conversation at a time. Egyptian regime couldn't control Revolutionaries. Open the following link and read the document compiled by Solidarity Movement for New Ethiopia in April 2012.
    http://www.solidaritymovement.org/amharic/120419TeleandINSA.pdf

    ReplyDelete
  2. Dear Solomon I thank you indeed, for the information.

    ReplyDelete