-ልዩ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ኃላፊነት ይኖራቸዋል
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ የመጀመሪያ ጉባዔ ሦስተኛውን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሹመት ያለ ድምፅ ቆጠራ በሙሉ መግባባት ሰይሟል፡፡
በዚህም መሠረት የረዥም ዓመታት የዲፕሎማሲ ልምድ ያካበቱትንና ኢትዮጵያን በተለያዩ አገሮች የወከሉትን ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ለቀጣይ ስድስት ዓመታት ሾሟል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የፕሬዚዳንቱን ሥልጣንና ተግባር በሚወስነው አንቀጽ እንደሚተነትነው፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዋና ሚና ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሔርነት መወከል በመሆኑ፣ የፕሬዚዳንትነት ኃላፊነት በርካታ ኢትዮጵያውያን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጡት ነው፡፡
የአገሪቱን ፕሬዚዳንት መምረጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ ኃላፊነት የተሰጠው ብቸኛው አካል ሲሆን፣ የአመራረጥ መስፈርትና መመዘኛው ደግሞ ከሕዝብ የተደበቀ በመሆኑ እስከ መጨረሻው ሰዓት የቀጣዩን ፕሬዚዳንት ማንነትን ማወቅ አልተቻለም፡፡
ባለፈው ሰኞ ከሰዓት በኋላ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ጉባዔን በይፋ የከፈቱትና ላለፉት 12 ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በዚሁ ዕለት ሥልጣናቸውን አስረክበዋል፡፡
ለቀጣይ ፕሬዚዳንትነት በብቸኝነት በአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ የተጠቆሙትና በሙሉ የምክር ቤቶቹ አባላት ይሁንታ የተሰየሙት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መሆናቸው፣ አነጋጋሪና በርካቶችን ያስገረመ መሆኑን ሪፖርተር ካነጋገራቸው ለመረዳት ችሏል፡፡
በብሔር ኦሮሞ የሆኑት ዶ/ር ሙላቱ የ56 ዓመት ጎልማሳና የአንድ ልጅ አባት ናቸው፡፡ ዶ/ር ተሾመ የገዢው ፓርቲ አባል በመሆን በርካታ ዓመታትን ያገለገሉ ሲሆን፣ በዋናነት በዲፕሎማሲው መስክ የበርካታ ዓመታት ልምድ አካብተዋል፡፡
ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን በመጣ ከሦስት ዓመታት በኋላ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን የዲፕሎማሲ ሥራቸውን መጀመራቸውን የሥራ ልምድ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በመቀጠልም በጃፓን የኢትዮጵያ ተቀማጭ አምባሳደር በመሆንና በተደራቢነትም በታይላንድ፣ በቬትናም፣ በኢንዶኔዥያ፣ በአውስትራሊያና በፊሊፒንስ ኢትዮጵያን በአምባሳደርነት ወክለዋል፡፡
በመቀጠል በሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በመጀመሪያ የቀድሞው የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ምክትል ሚኒስትር፣ እንዲሁም የግብርና ሚኒስትር በመሆን እ.ኤ.አ. እስከ 2001 ሠርተዋል፡፡ በኋላም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በድጋሚ ወደ ዲፕሎማሲ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
በዚህም መሠረት በቱርክ ቋሚ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆንና በተደራቢነትም የጆርጂያ፣ የአዘርባይጃን፣ የካዛኪስታንና የታጂኪስታን የኢትዮጵያ ተጠሪ አምባሳደር በመሆን እስከ ፕሬዚዳንታዊ ሹመታቸው ድረስ አገልግለዋል፡፡
ዶ/ር ሙላቱ በዲፕሎማሲው ዘርፍ በተለይ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገቡ መሆናቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህ ተግባራቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተምሳሌትነት ለሌሎች ዲፕሎማቶች የሚያነሳቸው ዶ/ር ሙላቱን እንደነበር ምንጮች በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረገውን …read more
Via: Ethiopian Reporter
No comments:
Post a Comment