ርሃብ፣ ድካም እና ሰቆቃው ለላፉት 12 ወራት ተፈራርቀውበታል። አንዴ በሰሃራ በረሃ ሌላ ግዜ ደግሞ በሜዲትራንያን ባህር የሰው አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ስቃይ አልፎ እግሩ አውሮፓን ምድር ከረገጠ እነሆ አንድ ሌሊት አለፈ። ሰነድ ገብረጻድቅ ይባላል። ፊቱ እጅግ ተጎሳቅሏል። ከሰውነቱ ላይ አጥንቶቹ ይቆጠራሉ።
ወጣቱ ተስፋ ወዳደረገባት የአውሮፓ ምድር ለመግባት የተነሳው ከአመት በፊት ነው። እንብርቱ የተቀበረችበትን ሃገር ተሰናብቶ ከወጣ ጀምሮ የደረሰበት መከራ ይህ ነው አይባልም። ሰነድን እመንገድ ወድቆ ነበር ያገኘሁት። ለጥቂት ደቂቃ አነጋገርኩት። ንግግሩ የሚረብሽ ነው። አጭር የቪዲዮ ቆይታችንን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።
No comments:
Post a Comment