Sunday, October 13, 2013

ጋንጃ በፌዴራል …..የናይጄሪያ ደጋፊዎች…ጨዋታዉ በቀጥታ አይተላለፍም!


ቀደም ብዮ የማሪዋና ምስል ስላለዉ የኢትዮጲያ ቡድን አርማ ነግሬያችሁ ነበር፤አዲስ አበባ የሚገኙ ሬድዮዎች ሳይቀሩ ይህንን ነገር አወገዙ፤በነገራችን ላይ ከ2ት ሳምንት በፊት ይህንን ነገር አስተዉሎ የነገረኝ ባልደረባዮ በክሪ ነበር፤እናም ዋናዉ ነገር ዛሬ ከ6ሰአት ጀምሮ ይህ ነገር ተከልክልዋል፤ፌዴራል ፖሊሶች የአፍሪካ ህብረት መሪዎችን ስብሰባ ከማቀላጠፍ ጎን ለጎን ይህንን አርማ የሚሸጡ ሰዎችን መያዝና መቀማት ጀምረዋል፤ይህ አሪፍ ነገር ነዉ..በተቻለ መጠንም ይህንን ለብሰዉ የሚሄዱ ሰዎችን እያግባቡ ሲያስወልቁ ነበር፤ነገ ስታድየም ዉስጥ ተመሳሳይ አይነት ነገር ሊኖር እንደሚችል ጠቋሚ ነዉ!!አስቀድሞ ሰዉ ይህንን ነገር እንዳይገዛ ቢያደርጉ ሰዉን ከወጪ ይዳርጉት ነበር፤
ናይጄሪያዎቹ ንስሮች ከራሳቸዉ ጥላ ሳይቀር የተደበቁ ነዉ የሚመስሉት..10 ሰአት አከባቢ የተወሰኑ ደጋፊዎቻቸዉ ተጫዋቾቹ ያረፋት ቸርችል ሆቴል ነዉ በሚል በእግራቸዉ ሲያቀጥኑት ነበር ዳገቱን..ያን ሰአት ደግሞ ተጫዋቾቹ ቦሌ ከሆቴላቸዉ ወደ ስታድየም እየሄዱ ነበር፤ልምምዱም ቢሆን የተደረገዉ በዝግ ስታድየም ነዉ፤ደጋፊዎቹን በተመለከተ –ዱርዱር ባንድን –ነዉ የሚመስሉት..ያልያዙት የሙዚቃ መሳሪያ የለም..ቦሌ ሲደርሱም ይህንን 1..2..3..ሙከራ የተባለ ይመስል እንመቀወጥ አድርግዋቸዋል፤ነገ በግራ ጥላ ፎቅ እንደሚገቡም ይጠበቃል፤
አሁን አንድ ነገር በጉጉት ለማንበብ እየገሰገሳችሁ እንደሆነ እገምታለሁ፤አዎ ጨዋታዉ በቲቪ አይተላለፍም፤ምክንያት ስፖርት 5 የተባለዉ የምስሉ ባለቤት 500ሺ ዶላር አምጡ ስላለ ነዉ፤እናም ናይጄሪያዉያን በጣም ተበሳጭተዋል፤አይዝዋችሁ የማይተላለፈዉ ወደ ናይጄሪያ ነዉ እንጂ እዚህማ በሚገባ ይታያል፤ልክ እንደኮንጎዉ ጨዋታ ክፍያዉ በድንገት ከፍ ብልዋል፤እናም ለመልሱ ጨዋታ ከወዲሁ ማሰብ ያሥፈልጋል፤
አሁን ይህንን የምጽፈዉ ሳሮ ማሪያ የናይጄሪያዎቹ ሆቴል ነዉ፤እናም አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አስተናጋጅ ጠጋ ብለዉ.እንደዉ ፉከራቸዉ አኮ አይጣል ነዉ.ሊፍቱ ላይ አኮ ስንገናኝ..its easy easy….we beat u..አልኙኮ..ብለዉ በምሬት ተናገሩ!!ጥዋት ቦሌ ደጋፊዎቹ ጣታቸዉን እያሳዩ 3 እና5 እናገባለን ሲሉ ነበር፤ናይጄሪያ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ዋልያን አሸንፎ አያቅም..ነገሩ በንደዚህ አይነት ግምቱ 1ኛ ደረጃን በያዘ ጨዋታም አልተገናኙም..ነገሩን በደንብ ስታስተዉሉት ከ93ቱ ቡድን ጋር ይመሳሰላል፤ያኔ የነ ያኪኒ ቡድን ቱኒዚያ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ እዚህ አዲስ አበባ ላይ በተስፋዮ ኡርጌቾ(አሁን አሜሪካ ይገኛል) ግብ 1ለ0 ተሸንፎ እዛ 6ለ0 አሸንፎ አለፈ፤ከዛ የአፍሪካ ዋንጫ በላ..ከዛም በአሜሪካኑ የአለም ዋንጫ ተሳተፈ..መመሳሰሉ ታድያ የአፍሪካን ዋንጫ መብላቱ..ከዛም ለአለም ዋንጫ….ነገ በከፊል ይለያል!!
ሞሰስና ጆን ኦቢ አንድ ክፍል ነዉ የያዙት፤ትዊን ቤድ ነዉ አይደል የሚባለዉ..ሎ…እናም ሲበሉም ሲሄዱም አንድ ላይ ናቸዉ፤ያዉ የባንክ አካዉንትና አንድ ቡድን መጫዋት ነዉ ያግባባቸዉ!!እናም ሌለቹ ጋር እምባዛም ግንኙነታቸዉ የላላ ነዉ ፤ልክ ሜዳ ዉስጥ እንደሚጣሉት!!
source .ethiotube

No comments:

Post a Comment