ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ሊያስር መሆኑ መረጃዎች አመለከቱ፤ (የሤራው_ጥንስስ_ጀመረ )
ሰማያዊ ፓርቲ በተከራየው ቢሮ ምክንያት ከፖሊስ ጋር ወዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን ተከራይ ነኝ ባዩ ግለሰብ «በሩ ላይ የሰቀልኩትን ባነር በጥሰውብኛል» ብሎ ኢንጂነሩ ላይ ክስ የመሰረተ መስርቷል። ፖሊስም የሰማያዊን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃልን ለማሰር እንቅስቃሴ የጀመረ መሆኑ ታውቋል። ኢ/ር ይልቃል ግን በቤተሰብ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆናቸው ተሰምቷል።
ይህበእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ የተከራየው ቢሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ፖሊስ ሕግን ጥሶ ፅ/ቤቱን መጀመሪያ ተከራይቼዋለው ለሚለው ግለሰብ እቃ እንዲያስገባና እንዲያስወጣ የፈቀደለት ሲሆን ዛሬ ጠዋትም እቃ ሲያስወጣና ሲያስገባ ታይቷል።
በ13/2/06 የቤቱ አከራይና ተከራይ ነኝ ባይ 5 ኪሎ በሚገኘው መናገሻ ፍ/ቤት በታርጋ ቁጥር (ኮድ 4 02612) በሆነ የመንግሥት ፒክአፕ መኪና ሲመላለሱ የነበረ ሲሆን ይህም የህዝብን( የመንግሥትን) ንብረት ካድሬዎች «ህጋዊ ፓርቲዎችን ለማኮላሸትና ለግል ጥቅማቸው እንዴት እየተጠቀሙ እንደሆነ ያሳያል» ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።
ኢንጂነር ይልቃል በወያኔ ፍረሃት በተጨናገፈውና አስደሳች በነበረው ሰልፍ ወቅት የወያኔው ጋዜጠኛ ለጠየቃቸው ጥያቄ «በቅርቡ ሴራ ጠምጥማችሁ ታስሩኛላችሁ፤ ግን ከትግላችን ልታቆሙን አትችሉም፤ እኛ ብንታሰርም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በቅርቡ ነፃነቱን ያውጃል» ማለታቸው አይዘነጋም።
ፎቶ 1 የሰማያዊ ፓርቲ በር ላይ የተለጠፈው ባነር
ፎቶ 2 የአከራይ መታወቂያ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ካደረጉት ውል ላይ የተነሳ
ፎቶ 3 የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮን ተከራይቼዋለው የሚለው የገዢው ፓርቲ ካድሬ
#ሴራው_ተጀመረ — with Ethiopian Mitmita
No comments:
Post a Comment