Friday, October 4, 2013

ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው


መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ 2005 የስራ አፈጻጸምና 2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል።
በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ የነበረው ስብሰባም እንዲሁ በተመሳሳይ ተቃውሞ መጠናቀቁን በውይይቱ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ በርካታ አጀንዳዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጉዳዮች ተሰብሰባዊውን በከፍተኛ ሁኔታ አወዛግበዋል።
2006 ዓም የጸረ ሰላም ወይም የጥፋት ሀይሎችን ማምከን የሚል በእቅድ እንዲካተት በቀረበው አጀንዳ ላይ ጸረ ሰላም ማን ነው የሚለው ጥያቄ በተሰብሳቢው ተነስቶ የመድረኩ መሪዎች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል። የዞኑ የጸጥታ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ /ማርያምነሀሴ ወር ገደማ 30 የሚሆኑ ሰዎች በጎንደር ከተማ ህዝቡን ተነስ በማለት ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሰዎች ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው።በማለት አንድነት ፓርቲ በጎንደር ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምሳሌነት አንስተዋል።
ሌላው የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ገዛሀን ተክሌ በበኩላቸውየኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጠ ብሎ መናገር ጸረ ሰላምነት ነውሲሉ አብረራርተዋል። ባለስልጣኑ አክለውም ህገመንግስቱን ለመጣስ የሚነሳ ሁሉ ጸረሰላም ተብሎ ይፈረጃል ብለዋል።
የጸጥታ ጉዳዮች ዘርፍ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ደግሞከመድረክ አፈንግጦ መውጣትና ሳያስፈቅዱ መናገር፣ ሳያስፈቅዱ ጽሁፍ መጻፍና ማሰራጨት፣ ሳያስፈቅዱ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ በጥፋት መልእክተኝነት ያስፈርጃል ሲል ገልጸዋል።
አቶ ፈንታ የተባሉ ባለስልጣንም እንዲሁየጎንደርን መሬት ኢህአዴግ አሳልፎ እየሰጠ ነውብሎ መናገር ጸረ-ሰላም ተግባር ነው በማለት የራሳቸውን ትርጉም አቅርበዋል።
ስለ ጸረ ሰላም ሀይሎች፣ አክራሪነትና ሽብረተኝነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ትምህርት እንዲሰጠጥ በቀረበው ሀሳብ ላይ ደግሞ በስብሰባው የተሳተፉ ተቃውሞአቸውን ገልዋል። ተሳታፊዎቹ 15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ስለ ሽብረተኝነት፣ አክራሪነትና ጸረሰላም ሀይሎች ማስተማር በህጻናቱ ላይ የስነልቦና ጫና ይፈጥራል በማለት ተከራክረዋል።
ሌላው አወዛጋቢ የነበረው ነጥብኢህአዴግ 2006 እቅድን ተቋሞችን በድርጅት አባላት በመሙላት እናሳካለን በማለት ያቀረበውሲሆን፣ ተሰብሳቢዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሁሉ በድርጅት አባላት ከሞላችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን ምን ልታደርጉዋቸው ነው?” በማለት ጥያቄ አንስተዋል።
ለሱዳን ተላልፎ የተሰጠውን መሬት በተመለከተ የአካባቢው ሰራተኞች የሁለቱን አገሮች ድንበሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆኑ በኢህአዴግ የቀረበውን ማስጠንቀቂያ አልተቀበሉትም።

No comments:

Post a Comment