Tuesday, October 22, 2013

በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ሁለት ወረዳዎች ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ እንዳለ ተጠቆመ

አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ስር ነበሩ፡፡ ነገር ግን መሬቱ ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ገበሬዎቹም አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ስብሰባ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ የጀመሩ ሲሆን ከ500 ሺህ ብር በላይም ለጉዳዩ ማስፈፀሚያ ማዋጣታቸው ተጠቁሟል፡፡ የአማራ ክልል እንኳ እምቢ ቢላቸው በፌዴራል እንደሚያስጨርሱም ተጠቁሟል፡፡
ነገር ግን የሳንጃ፣ ጠገዴ፣ ዳባትና አፎኛ ደምቢ ወደራ ነዋሪዎች የገበሬዎቹን ጥያቄ እንደሚቃወሙ የጠቀሱ ሲሆን ጥቅምት 12 በሚጠሩት ስብሰባም የንግድ ተቋማት እንደሚዘጉ፣ ስራ እንደሚያቆሙና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሚዘጉ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5792#sthash.3r3F85uz.dpuf

No comments:

Post a Comment