ከርዕሶም ኃይለ
ፕ/ት ሆነው የተመረጡት ሙላቱ ተሾመ ትምህርታቸውን በሰባዎቹ አመታት የተከታተሉትና “ዶ/ር” የሚል ማእረግ ያገኙት በቻይና ነው። በትምህርታቸው በጣም ደካማ ነበሩ። ሙላቱ ሁለት አመት ወድቀው ከመባረር የተረፉት በነዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አማካይነት ሲሆን፣ በወቅቱ ዶ/ር ነጋሶ ያሉበት ኮሚኒቲ ለዩኒቨርሲቲው ያቀረቡት የextension ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ መቀጠል እንደቻሉ፣ እንዲሁም ቻይና በነበሩ ጓደኞቻቸው እገዛ ለመጨረስና “ዶ/ር” ለመባል እንደበቁ፣ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምሁር በወቅቱ አጋልጠው ነበር። ምሁሩ ጉዳዩን ለማጋለጥ የተነሱት ዶ/ር ነጋሶ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቀረባቸውን ተከትሎ በስብሰባ ላይ « መንግስቱ ሃ/ማሪያምን መሰልከኝ» ሲሉ አቶ መለስ ዜናዊን ተናግረው ስብሰባውን ጥለው በመውጣታቸው፣ ከዚያም ዶ/ር ሙላቱ በያዙት አቋምና ጭራሽ «ነጋሶ መጠየቅና መታሰር አለበት» በማለት ከመለስ ወግነው በመናገራቸው ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል። ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ የረዷቸውና የኦ.ህ.ዴ.ድ አባል እንዲሆኑ ያደረጓቸው ዶ/ር ነጋሶ ሆነው ሳለ፣ ያን ሁሉ ውለታ ረስተውና በአደርባይነት ተሰልፈው እንዴት «ነጋሶ መታሰር አለበት» ብለው በጭፍን ይፈርዳሉ?..ሲሉ ምሁሩ በግርምት በወቅቱ ጠይቀዋል። ለአቶ መለስ ባሳዩት ታማኝነት ዶ/ር ነጋሶን ተክተው ፕ/ት እንዲሆኑ በወቅቱ ታጭተው የነበረ ቢሆንም፣ እንዲሰረዝ የተደረገው «የፓርቲ አባል ያልሆነ ነው ፕ/ት መሆን የሚችለው» የሚልና በተጨማሪ የቀድሞውን ፕ/ት ዶ/ር ነጋሶን ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርግ አሳፋሪ ህግ በመለስ እንዲወጣ በመደረጉ ነበር። ሌላው አነጋጋሪ ነጥብ ይህ አዋጅ ሳይሻር፣ ማለትም « የፓርቲ አባል ያልሆነ ግለሰብ ፕ/ት ይሆናል» የሚለው ህግ በአዋጅ ሳይሻር፥ የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ሙላቱ ተሾመ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው አስገራሚና ምን ያክል ለራሳቸው ህግና አዋጅ እንደማይገዙ የሚያሳይ ሆኗል።
ዘ-ሐበሻ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ናት።
በሌላም በኩል “ዶ/ር” ሙላቱ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ መጋቢት 1996ዓ.ም ፓርቲው ባደረገው ግምገማ በአቶ መለስ ከተዘለፉት አንዱ ሲሆኑ፣ ጉዳዩን በመንተራስ «ኢትኦጵ» ጋዜጣ «ከሕወሐት መንደር ከቃረምኩት» በሚል አምዱ በወቅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንደዘገበው፥ « አቶ መለስ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ “ ሙላቱ – አንተን ሚ/ር አድርጌ መሾሜን ረስቸዋለሁ። ያለስራ በሚ/ርነት የተጎለትክ ነህ፤ እዛው ጃፓን አምባሳደር እንደሆንክ ብትቀር ይሻላል። ..ኦ.ህ.ዴ.ድ ማለት ለትግል ፈጥረነው የት እንደገባ የማይታወቅ ድርጅት ነው።” » በማለት መለስ ዜናዊ መናገራቸውን አመልክቶ ነበር።
የ“ዶ/ር” ሙላቱ ባለቤት ወ/ሮ መአዛ አብርሃም ትባላለች። ሸንቃጣዋና የደስ ደስ ያላት መአዛ አንድ ጃፓናዊ አግብታና ልጅ ወልዳ በቶኪዮ ከተማ ትኖር ነበር። እራሷን በጣም ስለምትጠብቅና አለባበሷን (አጭር ሚኒ ቁምጣ ነው የምትለብሰው) ለተመለከታት በወጣትነት የእድሜ ክልል እንደሆነች አድርጎ ይገምታታል፤ ሃቁ ግን ወ/ሮ መአዛ 53 አመት እድሜ ይሆናታል። ከሙላቱ ተሾመ ጋር የተዋወቁት ጃፓን ነበር። መአዛ በጣም ብልጥ ሴት ናት። በጃፓን የኢትዮጲያ አምባሳደር የነበሩት ሙላቱ ተሾመን ታጠምዳለች። ያጠመደችው ወላጅ አባቷ አቶ አብርሃም ነጋ በቀይ ሽብር ወንጀል ተከሰው ስለታሰሩ ነበር። ጃፓናዊ የልጇን አባት ባሏን በመግፋት አምባሰድሩን ትቀርባለች። እንዳጋጣሚ አቶ ተሾመ የስራ ጊዚያቸውን ጨርሰው አገር ቤት ሲመጡ አብራ ትመጣለች። ክዛም ወላጅ አባቷን እንዲያስፈታላት ትጠይቃለች። የተጠየቁት ሙላቱ « ይህን በጭራሽ አልችልም። እነመለስ ከሰሙ ከእንጀራዬ ወዲያው ያባርሩኛል። ይህን ጥያቄ ዳግም እንዳትጠይቂኝ።» ይላሉ። ወላጅ አባቷ በ2000ዓ.ም ከእስር ተፈቱ። ወ/ሮ መአዛ ጃፓናዊ ባሏንና ልጇን በመተው ለፈፀመችው የትዳር ማፍረስ ተግባር ወደዛች አገር ዳግም እንዳትገባ ውሳኔ ስለተላለፈባት፣ ከ”ዶ/ር” ሙላቱ ጋር መጠቃለልን መረጠች። መአዛና ሙላቱ አንድ ልጅ አፍርተዋል። ሙላቱ ተሾመ በ1994ዓ.ም በሰባት ሚሊዮን ብር በቦሌ ያስገነቡት ዘመናዊ ቪላ በወር 36ሺህ ብር እንደሚከራይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ ቪላውን ለመገንባት ገንዘቡ በሙስና እንዲገኝ ትልቅ ሚና የተጫወቱት ባለቤታቸው ወ/ሮ መአዛ መሆናቸው ታውቋል።

No comments:
Post a Comment