Wednesday, January 1, 2014

የኢትዮ እስራኤላዉያን ህይወት

ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያን ለዘመናት ወደናፈቋት እስራኤል በብዛት መሄድ ከጀመሩ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሆኗል። እስከዛሬም ወደመቶ ሰላሳ ሺህ የሚበልጡ እስራኤል እንደገቡ ይታመናል።
ዛሬም ከኢትዮጵያ ወደዚያም ለመሻገር ተራቸዉን የሚጠብቁት ቁጥራቸዉ ቀላል አይደለም። ያም ሆኖ እዚያ የደረሱት በተለያዩ ምክንያቶች ከቀሪዉ አይሁድ እስራኤላዊ ጋ ተዋህዶ ለመኖር መቸገራቸዉ፤ አድሎም እንደሚገጥማቸዉ ይሰማል። ኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያኑ ችግሩን ይፋ አዉጥተዉ መፍትሄ ስለማፈላለጋቸዉ፤ ለመብታቸዉ መከበርም ስለሚያደርጉት ጥረት የሚባል የለም። ዶቼ ቬለ ሶስት እንግዶች ጋብዞ በእስራኤል የኢትዮ እስራኤላዉያኑን የኑሮ ሁኔታ የተመለከተ ዉይይት አካሂዷል።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

http://www.dw.de/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%8A%A4%E1%88%8B%E1%8B%89%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%88%85%E1%8B%AD%E1%8B%88%E1%89%B5/a-17314806

Breking News!!…News Alert!!…about Teddy Afro and Bedele beer.

Breking News!!…News Alert!!…about Teddy Afro and Bedele beer.
wede feker guzo the large music concert of teddy afro with Heinken beer and Bedele beer cancelled. the concert will be desired by the Bedele beer of the teddy afro concert cause of different problems the concert cancelled on the situation Bedele and Heinken management chief executive officers will be gives press release tomorrow in Addis Ababa. but all the Teddy Afro fans and the entertainment family admired teddy and Bedele patience of the situations also the brewery company of Bedele officials to success of the concert do everything but it is failed. we will report more news about the situation soon!!
via:http://www.harartubes.com/

በኢትዮጵያ የተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እየከለከሉን ነው ሲሉ 18 የቻይና ኩባንያዎች አመለከቱ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል።                         ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው ጋዜጣው፣ በእነዚህ የመሠረተ ልማት ዘርፎች የተሰማሩት የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰኑ ባለሥልጣናት ቀደም ብለው ለገቡ የቻይና ኩባንያዎች ያለ ውድድር ሥራ እንደሚሰጡዋቸው፣ ደካማ የሥራ አፈጻጸም እያለባቸውም አንዱን ሥራ ሳይጨርሱ ተጨማሪ ሥራዎችን በላይ በላዩ ይሰጧቸዋል የሚል ቅሬታቸውን ዘርዝርው ለመንግስት አቅርበዋል።

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ (ሄኖክ የሺጥላ)

ታላቁ የኢሃዲግ መንግስት ከሚከበርበትና ከሚወደስበት የቀለበት መንገድ በተጨማሪ (ግድቢ ኣደይ ሃዳስ (የእማማ ሃዳስ ግድብ) (ለመሃል ኣገር ሰው ይስማማ ዘንድ የህዳሴውን ግድብ እየተባለ የሚነገረውን ሳይጨምር…) ከሚታወቅበት ኣንዱ እንቅልፍን ያለ ገደብ መፍቀዱ ነው። በነገራችን ላይ ያባይ ቦንድ የብዙ ኣባወራዎችን ትዳር በማፍረሱ ያባይ ቦንብ የሚል ስም ሊሰጠው እንደሆነ ጥቃት ያደረሱትም ጥቃት የደረሰባቸውም እየተናገሩ ነው:: የዚህ ያባይ ቦንብ የሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑት ሰዋች እንደሚሉት ከሆነ ኣማሪካ ቢሆን disability ክሌም ኣርገን እንደ ኣካፋ ዝቆ በሚያነሳ ኣውቶብስ ፈልሰስ እያልን እንኖር ነበር፤ እኛ ግን ከጥቃታችን ሳናገግም፤ ተገድቦ የት ያደርሰናል ያልነው ኣባይ ጉሮሮዋችንን ገድቦ ይስረቀረቃል ብለዋል። ለነገሩ ኣባይ ኣፍ የለውም እንጂ ቢጠይቁት የደደቢት ድርዬዎች ሃንግ ኣረጉኝ ብሎ ለኣውሽና ቦርከና ይናገር ነበር። ምን ያረጋል ታዲያ ኣባይ እንኩዋን ኣፍ ማደሪያ የለውም። ኣባይ በስምሽ ስንት ታሪክ ተሰራ። ትገርሚያለሽ፤ በቃ ግንዱ ኣልበቃ ብሎሽ የዲያስቦራን ዶላር ትጠርጊ ጀመር፤ ለነገሩ ኣንቺ ምን ታረጊ፤ ሆዶ ነው ቁም ነገረኛ ያረገሽ እዚህ ዛሬ ከኛ ጋ ተቃውሞ ማታ ደሞ እትዮጵያ ደውሎ፤ እንዴት ነው ቦንዱ፤ ግድቡ እያለቀ ነው፤ ምን ይጠበቅብኛል ጌቶች የሚለው፤ ይሄ ሁለት ቢላ ህዝብ ኣባይዬ በናትህ በጣና ይሁንብህ፤ ይህንንማ ውስክስክ ላፍልኝ፤ መቅኖ ኣስቀረው፤ ኣላርፍ ያለ ዲያስፖራ ያባይ ቦንድ ይገዛል ኣሉ። …read more
Source: Ecadforum

በደቡብ ክልል የይርጋ ጨፌ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መምህራኑ አድማውን የጀመሩት ያለፍላጎታችን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደሞዛችን እየተቆረጠብን ነው በሚል ነው። መምህራኑ ለይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር፣ ለጌዲዮ ዞንና ልክልሉ ትምህርት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ” ከ ሀምሌ 2005 ዓም ጀምሮ ለህዳሴ ግድብ የሚቆረጠው ገንዘባችን እኛ ያለፈቀድነውና ያልተስማማንበት በመሆኑ ጥቅምት 28፣ 2006 ጀምሮ ስራችንን በአግባቡ እየሰራን የመብት ጥያቄያችንን ለሚመለከተው ሁሉ ስናቀርብ በመቆየታችን ታህሳስ አንድ በዞን መምህራን ማህበር ሰብሳቢነት የከተማው ከንቲባ ፣ የከተማው ትምህርት ዩኒት ሃላፊ በተገኙበት አቆራረጡ አግባብነት የሌለውና የመምህራንን መብት የጣሰ መሆኑን በውይይቱ ተረጋግጦ ከታህሳስ ጀምሮ የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲቆም፣ መወሰኑን” አስታውሷል። ድብዳቤው “ነገር ግን የከተማው አመራር እንደተለመደው በመዋሸት እንዲቆም የተወሰነው ገንዘባችን እንዲቆረጥብን አድርጓል” ይላል።

Toltu Tufa is OPride's Oromo Person of 2013

ToltuTufa n2(OPride) – For revitalizing Oromo language learning, for revolutionizing Oromo storytelling and inspiring others to look within themselves for "bold new ways" of telling their story, for awakening the Oromo Diaspora to rally behind Afaan Publications, for being the Oromo story of 2013, Toltu Tufa is OPride's Oromo Person of the Year.

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች በአዲስ አበባ ለመደራደር ተስማሙ

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች በአዲስ አበባ ለመደራደር ተስማሙ
በእርስ በርስ ግጭት ሳቢያ ቀውስ ውስጥ የምትገኘው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ፕሬዚዳንትና ተቀናቃኛቸው በኢጋድ ሸምጋይነት በአዲስ አበባ ድርድር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከሰሜንዋ ሱዳን ነፃ ከወጣች ሁለት ዓመት የሆናት ደቡብ ሱዳን፣ በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና በቀድሞው ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳው ቀውስ፣ የጐሳ ቅርፅ ይዞ ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ ከ200 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ተፈናቅለዋል፡፡
ችግሩን ለመፍታት በግንባር ቀደምትነት እየተንቀሳቀሰ ያለው ኢጋድ፣ ሁለቱም ወገኖች ተኩስ አቁመው ችግራቸውን በድርድር እንዲፈቱ ያስጠነቀቀ ሲሆን፣ ለዚህም የአራት ቀናት ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር፡፡

የሁዳ ሪል ስቴት ካርታ ቢመክንም መሬቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ አልሆነም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሼክ መሐመድ አል አሙዲ ኩባንያ ለሆነው ለሁዳ ሪል ስቴት ሰጥቶት የነበረው የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መምከኑንና መሬቱም ወደ መሬት ባንክ መግባት ቢኖርበትም፣ ኩባንያው ፈቃደኛ ሆኖ እንዳልተገኘ ምንጮች ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኅዳር 2005 ዓ.ም. የሁዳ ሪል ስቴት መሬት እንዲነጠቅ የጻፈውን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኘውን የኩባንያውን መሬት አምክኗል፡፡

ሥራ ማግኘት አልቻልንም ያሉ የቻይና ኩባንያዎች ቅሬታቸውን ለመንግሥት አቀረቡ

ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተን እንዳንሠራ እንቅፋት ተፈጥሮብናል የሚሉ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡ ኩባንያዎቹ የቅሬታቸው መሠረት የሆነው ቀደም ብለው ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች፣ ከአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር ሥራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል የሚል ነው፡፡

በህዳሴው ግድብ ላይ ግብፅ ያነሳቻቸው ጥያቄዎችና የኢትዮጵያ አቋም ለፓርላማ ቀረበ

- ግብፅ ግድቡን የሚከታተል ቢሮ በአዲስ አበባ ለመክፈት ጠየቀች:: የኢትዮጵያ ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የህዳሴው ግድብ ብሔራዊ የባለሙያዎች ቡድን ግድቡን በተመለከተ እያደረጉት የሚገኘውን ድርድርና በግብፅ በኩል እስካሁን እየተነሱ ያሉ ጉዳዮችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ቀረበ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑና በሚኒስቴሩ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ አነሳሽነት በተፈጠረው መድረክ የግብፅ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ የውኃ ሚኒስትሮች ግድቡን በተመለከተ መግባባት ላይ ለመድረስ በድርድር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡