by Abraha Desta
በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ እንገኛለን። የህዝብ ስብሰባው ለመጀመር አዳርሹ ሲከፈት ህዝብ በስብሰባው ለመሳተፍ መግባት ሲጀምር አስተዳዳሪዎቹ ደንግጠው ‘በስብሰባው መሳተፍ የሚችል ሰው የቀበሌ መታወቅያ ያለው’ ብቻ መሆን እንዳለበት አወጁ። መታወቅያው እየመዘገቡ ለማስገባት ወሰኑ። ህዝቡ ተቃወመ። የዓረና አመራር አባላትም ድርጊቱ ተቃወሙ። መታወቅያ የሌለው እንዳይገባ ስለተወሰነ ብዙ ሰው ተቃውሞ ስላነሳና መግባት ስለፈለገ የአዳራሹ መግብያ በር ተዘጋ። አሁን የተፈቀደልን አዳራሽ ዝግ ነው። ዓረና ስብሰባው በአዳራሹ በር ባለው ሜዳ ለማካሄድ ወስኗል። ባደራሹ በር አከባቢ ብዙ ህዝብ አለ። ካድሬዎቹ ህዝቡ ለመበተን እየፈተኑ ነው።
No comments:
Post a Comment