ERITREA/GINBOT 7 Via#Girum Zeleke#
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው የግንቦት የታጠቀ ቡድን በሰነይ በረሃ በኤርትራ ውስጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ በመክሸፉንና ታጣቂዎቹ ወደ ሱዳን የፖለቲካ ጥገኝነት እንደጠየቁ ተዘገበ። ግንቦት ህዝባዊ ሃይል በአሁኑ ወቅት ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ የሰራዊት አባላት ብቻ እንዳሉት ይህ የታመነው የዜና ምንጭ አስታውቋል።
ከሁለት ወር በፊት በፃፍኩት ተመሳሳይ ዘገባ በአደረጃጀት ችግር ምክንያት ከ120 በላይ የያዘ ህዝባዊ ሃይል ለማዋቀር አለመቻሉን በትንታኔ አቅርቤ ነገር ግን በቅርብ የማውቃቸው የድርጅቱ ደጋፊዎች በተለያዮ አልባሌ አነጋገሮች ዘገባውን የወያኔ ወሬ ነው ብለው አጣጥለውት እንደነበር ይታወሳል። የዜናው ምንጭ ከአለም ዲፕሎማቲክና ስለላ ማህበረሰብ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው The Indian Ocean Newsletter የአፍሪካ ኢንተለጀንስ ዜና አውታር ነው።
በ መስከረም 02/2013 የታላቋ ብሪታንያ የመከላከያ ሚኒስትር የበላይ አማካሪ የሊብራል ዲሞክራቱ ኒክ ሃርቬይ ከወያኔ የውጭ ጉዳይ ልኡካን ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ በኤርትራ አለ የተባለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደማያምኑበት ከታላቋ የብሪታንያ አለም አቀፍ ወታደራዊ ኢንተለጀንስ ቢሮ ባላቸው መረጃ ማወቅ መቻላቸውን አስረድተዋል።
ይህ እንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከድርጅቱ አመራር የአነጋገር ዘይቤዎች ሳይቀር ህዝባዊ ሃይል የማደራጀቱ ስራ ምንም ያክል እንዳልተራመደ የሚጠቁሙ መሆናቸው ግልፅ ነው። በመስከረም 28/2013 ኦስሎ ከተማ ከተደረገው የግንቦት 7 ሕዝባዊ ግንባር ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኋላ የግንቦት 7 ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ October 1, 2013 ለ ESAT በሰጡት መግለጫ በሕዝባዊ ግንባሩ ስም ከዚያን ቀን በኋላ ምንም አይነት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እንዳይካሄዱ ማዘዛቸው ሊዋቀር የታሰበው ሠራዊት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ ከጊዜ በኋላ ከሚመጣው ተጠያቂነት ለመዳን መሆኑ ግልፅ ነው።
"Andargachew Tsige, the Secretary General of the opposition Ginbot 7 Movement said that they are forming their own network within the Ethiopian Defense Forces. He said this after a successful fund raising event held in Norway over the weekend." .... "He also stressed that there should not be any fund raising event in the name of the Popular Force or individuals until the Force makes its own fund raising programs public in the future."
Source: http://ethsat.com/2013/10/02/g7-is-forming-a-network-within-the-defense-forces-andargachew/
The Indian Ocean Newsletter Dated 28/09/2013

No comments:
Post a Comment