የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በሚል ለሁለት መከፈሉን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አሁን ባለው አዲስ አደረጃጀት ኃይል አመንጪውና አገልግሎት ሰጪ የተለያየ ኩባንያ እንዲሆን የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት የግልገል ጊቤ ሶስት ፕሮጀክት ዋና ሥራአስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ መሆናቸው ታውቋል። ሁለተኛውን ማለትም የአገልግቱን ዘርፍ በማኔጅመንት ኮንትራት ደረጃ የሚመራው ፓወር ግሬድ የተባለው የህንድ ኩባንያ ነው።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ወደ 13ሺህ 375 አካባቢ ሰራተኞች የነበሩት መሆኑን ዶ/ር ደብረፅዮን አስታውሰው እነዚህ ሰራተኞች በአዲስ መልኩ በሚደራጁት ሁለቱም ኩባንያዎች ውስጥም በሥራቸው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ኩባንያዎቹ 4ሺህ100 ተጨማሪ የሰው ኃይል ክፍተት ስለሚታይባቸው በቀጣይም ሰፊ ቅጥር የሚያስፈልግ መሆኑን በማመልከት የሰው ኃይሉንም ክፍተት ለሚሟላት በቅርቡ ቅጥር የተጀመረ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ነባሩን ሰራተኛ ባለው የትምህርት ደረጃ፣ ልምድና ክህሎት በአዲስ መልኩ የመመደብ ስራ የተጀመረ መሆኑን በመግለፅ ይህም ከላይ የተጀመረው ምደባ ወደታች የሚወርድ መሆኑ ታውቋል።
No comments:
Post a Comment