Monday, March 3, 2014

ከጭሮ ከተማ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት ታሳሪዎች መካክለ ሼህ ሃሰን በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው ሂወታቸው ማለፉን ምንጮች አስታወቁ

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሃረርጌ በጭሮ ከተማ በሚገኙ ከተለያዩ ወረዳዎች በፖሊስ ተይዘው በጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት ለረጅም ጊዜ ታስረው ለህክምና ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት ታሳሪዎች መካክለ ሼህ ሃሰን በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው ሂወታቸው ማለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡
በጭሮ ከተማ ከተለያዩ ወረዳዎች በጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት ታስረው ባደረባቸው ከፍተ|ኛ ህመም ምክንያት ማረሚ|ያ ቤቱ ከአንድ አመት በፊት ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤት ወደሆነው ቃሊቲ ማረሚ|ያ ቤት ሪፈር በመፃፍ ወደ አዲስ አበባ ሄደው እንዲታከሙ ለማድረግ ሞክሮ ነበር፡፤ ሆኖም ታሳሪዎቹ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዞን 3 ታስረው የሚገኙ ሲሆን ምንም የረባ ህክምና ሳያገኙ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ምንጮች አስታውቀዋል፤፤
ከምዕራብ ሃረርጌ ጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከአመት በፊት የተዘዋወሩት ታሳሪዎቹ ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል
1. መሐመድ ሐሰን አሊዩ በምዕራብ ሀርርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ
2. መሃመድ አህመድ በምዕራብ ሀርርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ
3. ሼህ ሀሰን በምዕራብ ሀረርጌ ዳሮ ለቦ ወረዳ ገለሞተራ ቀበሌ
4. ከተማ ጸጋዬ መገናኛው በምዕራብ ሃረርጌ መቻሬ ወይም ገመቺስ ወረዳ ሽሬ ቡሉ ቀበሌ
5. ከተማ ለማ ኢሾ በምዕራብ ሃረርጌ መቻሬ ወይም ገመቺስ ሽሬ ቡሉ ቀበሌ
6. ዘውዱ ታሪኩ እንደሻው በምዕራብ ሃረርጌ ዳርጌ ሳውሮ ወረዳ ቀበሌ 34 ነዋሪ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዞን 3 ታስረው ከሚገኙት ታሳሪዎች መካከል በምዕራብ ሃረርጌ የጭሮ ከተማ የደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት ሼህ ሃሰን በማረሚያ ቤቱ በቂ ህክምና እንዳያገኙ በመደረጋቸው በየካቲት 15/2006 ሂወታቸው ማለፉን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ሼህ ሃሰን ከጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት በቂ ህክምና እንዲያገኙ በሚል አብረዋቸው ከታሰሩ ሌሎች ታሳሪዎች ጋር ወደ አዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቢዘዋወሩም ማረሚ|ያ ቤቱ ተገቢ እና በቂ ህክምና እንዳያገኙ በማድረጉ ከዚህ አለም በሞት ሊለዩ እንደቻሉ ታውቋል፡፡ የሼህ ሀሰን ቤተሰቦችም ሊያገኟቸው አለመቻላቸውን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይም ሁኔታ ሌላኛው በምዕራብ ሀርርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ ነዋሪ የነበረው እና የዞን 3 ታሳሪ የሆነው .መሐመድ ሐሰን አሊዩ በቂ ህክምና ባለማግኘቱ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
በኢትዬጲያ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ታስረው የሚገኙ ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በህክምና እጦት ምክንያት ሂወታቸው በስቃይ የሚያልፉ ታሳሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እየተሰማ ሲሆን የማረሚያ ቤቶቹ አስተዳደሮች ለሰው ልጅ ሂወት ክብር በመንፈግ ይህን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ የፖለቲካ መቅጫ ዘዴ አድርገው መቀጠላቸው ታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤትም ወረርሽኝ ገብቶ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውን |ጨምሮ በርካታ የማረሚያ ቤቱ ታሳሪዎች ለህመም ተጋልጠው እንደነበር ይታወሳል፡፤ በማረሚያ ቤቱ ባለው የንፅህና ጉድለት እና መጥፎ ሽታም ኮሚቴዎቻችንንም ጨምሮ ለከፍተኛ የሳይነስ እና ተዛማጅ በሽታዎች ተጋላጭ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ይታወቃል፡፡
ወደ አኼራ የሄዱትን ሼህ ሀሰንን አላህ ማረፊያቸውን በጀነት ያድርግላቸው!!
በመላው ሃገሪቱ ታስረው የሚገኙ ታሳሪዎችን አላህ በራህመቱ ይጠብቃቸው!!!
Source: Dargaggotta Oromoo Oslo
source:http://ayyaantuu.com/horn-of-africa-news

No comments:

Post a Comment