ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 20/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ባወጣዉ የዘንድሮ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያከናዉናቸዋል ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመዘርዘር ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቦታል።
ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል።
ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል።
በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ሳቢያ ዜጎች የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመናገር መብትን በገሃድ እንደሚነፈጉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ያስደረግቸዉን ጥናቶች ተመርኩዞ ያብራራል። እነዚህን የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመተግበር የሚሞክሩም ይታሰራሉ፣ይንገላታሉ፣ይዋከባሉ፣ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ክብራቸዉ ተነክቶ እንዲሸማቀቁምይደረጋሉ በማለት ሪፖርቱ ያትታል።እርዳታን የሚያስተባብሩ፣ እርዳታን ለጋሽ የሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበራዊና ትርፍ አልባ የሆኑ ተቋማት (NGO) የግብረ-ሰናይ ተልእኮ አቸዉን እንዳይፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚከለክል፤ በሰዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ግድያ እንደሚፈጽም፣ዜጎች ግርፋት-ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ፣ ወጥ የሆኑ የማሰቃያ ተግባራት በመንግስት ሐይላት እንደሚፈጽምና በአገሪቱ እስርቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጹ አሳቃቂ ተግባራትም እንዳሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
ሰዎች በፍርድ ቤት ሳይበየንባቸዉ በጅምላ ተይዘድዉ ይታሰራሉ፤በፍርድ ቤት የአሰራር ዘይቤም ይሁን በፍትህ ሒደቱ ዉስጥ ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት አለበት፤ ፍርድ ቤቶችም ደካማ ናቸዉ! ሲል ሪፖርቱ ይደመድማል። መንግስት ሀሳብን በነጻነት ለመግለጽ የሚሞክሩ ያገሪቱ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እንደሚወስድ በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን፤ በነሐሴ 2/2005 የኢድ-አልፈጥር በዓል በሚከበርበት ወቅት፤ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞ ያሰሙ ከነበሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን መካከል ከ 1000 በላይ የሚሆኑት በጅምላ ተግበስብሰዉ መታሰራቸዉና ከመካከላቸዉም የሞቱ መኖራቸዉ በሪፖርቱ ላይ አጽንኦት ተሰጥቶታል።የዜጎች ግላዊ መብትን በመግፈፍ፤ በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ ህገወጥ የሌሊት ፍተሻዎችም ተደርገዋል። ግልጽና ስልታዊ በሆነ መልኩም ከቦታ ወደ ቦታ ዜጎችን የማፈናቀል መርሃግብር በመንግስት መፈጸሙን የሚያስረዳዉ ሪፖርት ነጻ መሆን የሚገባዉ የመማርና የማስተማር ሒደት የመንግስት ጣልቃገብነት እንዳለበትም ይገልጻል።
ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸዉን ተጠቅመዉ በነጻነት መንግስትን የመቀየር አቅማቸዉ ሆን ተብሎ የተገደበ ነዉ!በፖሊስ፣በፍርድ ቤቶችና በመንግስት አመራር ዉስጥ በስልጣን መባለግ-ሙሰኝነት-ጉቦኝነት በገሃድ ይተገበራሉ። መንግስት በስልጣን የባለጉንና የህዝብን አደራ ያጎሳቆሉ ወንጀለኞች ችላ በማለት ፖለቲካዊ ዉለታን ይዉላል፤ ፖለቲካዊ ምህረትን ለምግባረ ብልሹ የመንግስት አካላት እንደሚያደርግ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ያጋልጻል።
በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የጾታ እኩልነት የተረጋገጠ ቢሆንም በመንግስታዊ የአሰራር መዋቅር ዉስጥ ሴቶች ይጨቆናሉ። ህገወጥ የሆነ የሰዉ ዝዉዉር ይፈሰማል፣ የአካል ጉዳተኞች (የተሳናቸዉ) ማህበራዊ ጭቆና ይደርስባቸዋል፣የ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህሙማን ማህበራዊ የሆነን በደል ይጋፈጣሉ፣የሰራተኖች መብት የተገደበ በመሆኑ ህፃናትን አስገድዶ የጉልበት ስራ ማሰራቱ የተለመደ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተዘርዝሯል።
የመንግስት ሐይላት የሰዎችን ደብዛ ያጠፋሉ፤ የሰዎች መሰወር ይስተዋላል! በትግራይ ክልል በአላማጣ ከተማ መንግስት በልማት ስም ቤቶችን በሚያፈርስበት ወቅት አለመግባባት ተፈጥሮ የታሰሩ 12 የአካባዊ ተወላጆች የገቡበት እንደማይተዋቅ እና ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በሶማሌ ክልል ያለዉ ልዩ የፖሊስ ሐይል በክልሉ ተወላጆች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ማንገላታት፣ማሰቃየት፤ ግድያ እደሚፈጽም መታወቁ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ህገመንግስት ቶርቸር (ግርፋት ድብደባ ማሰቃየት)ይከለክላል። ቶርቸርን የመሰሉ የሰዉ ልጅን ክብር ገፋፊ የሆኑ ጭካኔ የተሞላባቸዉ ተግባራት፤በመንግስት የደህነነትና የጥበቃ ሐይላት እንደሚፈጸሙ በማጋለፅ በጥር 9/2005 የተያዘዉ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት አምድኛ እና ማኔጂንግ ኢዲተር የነበረዉ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ በተደጋጋሚ የዚሁ ህገወጥና አስከፊ ተግባር ሰለባ እንደነበር በዩናይትድ እስቴት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ላይ በዋቢነት ተጠቅሷል።
በጥቅምት 8/2006 ሁማን ራይትስ ዎች ያወጣዉን ሪፖርት እንደ አብነት በመጥቀስ በመጥቀስ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ መርማሪዎች ታሳሪዎችን በማስገደድ የእምነት ቃል እንደሰጡ እንደሚያደርጉ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እየገለጸ፤ በማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር (ግርፋት-ድብደባ-ማሰቃየትት)፣ ዛቻ፣ማስፈራራርት፣ እስረኞች ላይ ዉሃ መድፋት፣የእስረኞችን እጅ ጣራ ላይ አስሮ ለረጅም ሰዓታት ማቆም፣እሰረኞችን ነጥሎ ለብቻ ማሰርን የመሳሰሉ ኢሰብዓዊ ተግባራት እንደሚፈጽሙና ዲፕሎማቶች፣ኤንጂኦ (በጎ አድራጊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ትርፍ አልባ ድርጅቶች) እስረኞችን የመጎብኘት ፍቃድ እንደሚነፈጉ ተገልጿል።
በመስከረም 2005 በተገኘዉ መረጃ መሰረት ከ70,000 እስከ 80,000የሚድርሱ እስረኞች መኖራቸዉ ሲታወቅ፤ ከነዚህም መካከል 2500ሴቶች ሲሆኑ 600 ህጻናት ከእናቶቻቸዉ ጋር መታሰራቸዉ እና ታዳጊ ወጣቶች ከአዋቂዎች ጋር አብረዉ እንደሚታሰሩ ተዘግቧል። የአገሪቱ እስር ቤቶች በጣም የተጣበቡ ከመሆናቸዉም ባሻገር ወታደራዊ ተቋማትም እንደ እስር ቤት ማገልገላቸዉ ተዘግቧል። በርካታ እስረኞች ከመጣበብ፣ተነጥሎ ከመታሰር፣ የተማሏ የጤና ግልጋሎት ካለመኖሩ የተነሳ ለአእምሮ ህመም ይዳረጋሉ። ለአንድ እስረኛ የምግብ፣ የዉሃ አቅርቦትን ለመለገስ እና የጤና ግልጋሎት ለመስጠት በቀን ስምንት ብር ከአስር ሳንቲም ብቻ እንደተመደበ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አመታዊ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ይዘረዝራል።
ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ከ2004 ጀምሮ ሰላማዊ የሆነ ተቃዉሞን በአወሊያ የትምርት ተቋም ዉስጥ በመጀመር ከአርብ ስግደት (ከጁመዓ ሶላት) በሗላ በቀጣይነት የተቃዉሞ መርሃግብር እንደሚያከናዉኑና፤ ይህ የቅዋሜ ተግባር ምንም ሰላማዊ ቢሆንም የፖሊስ አካላት ሰዎችን በመያዝ አላስፈላጊ ሐይል እንደሚጠቀሙ ሪፖርቱ ያስረዳል። በሐምሌ 14/ 2004 በሙስሊሞች የተደረገዉን ሰላማዊ ተቃዉሞ ተከትሎ መንግስት “የደህንነት ሰጋት” የሚል ማመካኛን በመፍጠር 28 ሙስሊሞችን አስሮ በጥር 24/2005 ክስ ያቀረበባቸዉ ቢሆንም በታህሳስ 3/2006 አስሩን በነጻ አሰናብቶ በአስራ ስምንቱ ላይ ያቀረበዉን ክስ ዝቅ አድርጓል። መንግስት እነዚህን የሙስሊም ታሳሪዎች በአለማችን ላይ ከሚታወቁ አሽባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብሎ በገሃድ ለመፈረጅ መሞከሩም በሪፖርቱ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት የመናገር-የመደራጀት-የመሰብሰብን መብት የሚተገብሩ ፖለቲከኞችናና ጋዜጠኞችን እንደሚያስር፣ እንደሚያሰቃይ፣ እንደሚያንገላታ፣ የሚገልጸዉ ሪፖርት ከፖለቲከኞች የመድረኩ አንዱአለም አራጌ ብሎም የኦሮሞን ማህበረስብ መብት በዲሞክራሲ ለማስከበር ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ተወላጆች በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳ ታስረዉ እየተሰቃዩ መሆናቸዉን፤ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ከጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ሪዮት አለሙና ሰለሞን ከበደ በእስር ይማቅቃሉ ሲልም ሪፖርቱ ያስረዳል።
መንግስት ነጻ-ፕሬስ እንዲከስም በሚያደርገዉ ከፍተኛ ጫና ጋዜጠኞች የእስርና የስደት ሰለባ መሆናቸዉ ቢታወቅም፤ዳግም መንግስት የአፈና መረቡን በመዘርጋት የኢንተርኔት፣ የሳተላይት-ቴሌቭዥን ስርጭትን፣የማህበራዊ መገናኛ መደረኮችን፣የድረ ገጽ የመረጃ አዉታሮችን በማወክ ህዝቡ ማግኘት የሚገባዉን መረጃ ከማፈኑም ባሻገር፤ የጋዜጠኖች፣ የፖለቲከኞች እና የአክትቪስቶችን ኮምፒዉተር ለመሰለል ህገወጥ የሆነ የኮምፒዉተር ቫይረስን መንግስት እንደሚልክ ሲት ዝን ላብ (citizen lab) የተባለዉን ድርጅትን መረጃ ዋቢ ያደረገዉ የዩናይትድ እስቴትስ አመታዊ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት የህዝብ የሆኑ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን ሙሉ በሙሉ ተጠቅሞ ለፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳ እየተገለገለባቸዉ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
Source: Zehabesha
No comments:
Post a Comment