(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ ከተዘጋ 3 ቀን እንደሞላው በአካባቢው የከባድ ሹፌር አሽከርካሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። እነዚህ ሹፌሮች እንዳስታወቁት ይህ መንገድ የተዘጋው የከባድ መኪና ሹፌሮች ባደረጉት አድማ የተነሳ ነው።
ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያቀበሉት ሹፌሮች እንደገለጹት ለከባድ መኪና አሽከርካሪዎቹ የሥራ ማቆም አድማ ምክንያት የሆነው አንድ ሹፌር ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መንገድ ላይ በመገኘቱ የተነሳ ነው። በገዋኔ አካባቢ ይህ መንገድ እንደተዘጋ የገለጹት ሾፌሮቹ መንገዱ በመዘጋቱ የተነሳ የቆሙት መኪኖች ብዛት በኪሎ ሜትር እንደሚቆጠር አስታውቀዋል።
የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት እነዚሁ ሹፌሮች ጥያቄያቸው የደህነንት ዋስትና እንደሆነ የገለጹት ምንጮቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ተከበው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
Source: Zehabesha
No comments:
Post a Comment