ኢትዮጵያውያን በተጠንቀቅ ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል። የዲፕሎማቲክ ጫናዎች እየተደረጉ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከፖሊስ ጋር አፈሳውን ተከትለው ተጋጭተዋል። ፖሊስ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበትን አካባቢ ሰርጎ በመግባት ከኤምባሲ ዲፕሎማቶች የደረሰውን መረጃ በመያዝ ገጀራ እና ቖንጨራ ታጥቀዋል ወደተባሉት ኢትዮጵያያን መኖሪያ ከበባ ያካሄደ በመሆኑ ይህ ግጭት ሊቀሰቀስ እንደቻል የአረብ ኒውስ ጋዜጠኞች በሰበሰቡት መረጃ ጠቁመዋል።
በዚህ መልኩ በተደረገ ግጭት አራት ኢትዮጵያውያን እስካሁን ሲሞቱ አንድ የሳኡዲ ዜጋ ሞቷል። ከ ሰባ በላይ ሰዎች 28 ሳኡዲዎችን ጨምሮ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 104 መኪናዎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። በወቅቱ ፖሊስ 516 ኢትዮጵያውያንን ይዟል። ኢትዮጵያውያን ገጀራ እና ቆንጨራ ታጥቀዋል በማለት የገዛ ዜጎቹን ስም ያጠፋው የወያኔ ኤምባሲ ሊጠየቅ ይገባዋል። ትላንትና በድብቅ ሪያድ ገብቶ እንደ ተራ ሰው ወደ ሆቴሉ የሄደው ቴዎድሮስ አድሃኖም ዛሬ በአረብ ሊግ ግፊት የሳኡዲ ባለስልጣናት እንዳናገሩት ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል። ጭፍጨፋው ከተደረገ ከ 4 ቀን በኋላ ለውጭ ጉዳይ ጌቶቹ ሪፖርት ያደረገው እና የተመዝገቡ ወረቀት የለጠፈው የወያኔ ኤምባሲ ለዜጎቹ ደንታ እንደሌለው በገሃድ አስመስክሯል።
ለቀድሞው ሆድ ኣደር ፕሬዚዳንት ለነበረው ግለሰብ የ4መት ሺህ ብር ቤት ለምን ተከራየን እያሉ ሲሞግቱ የነበሩት የወያኔ አደናጋሪ ካድሬዎች የሳኡዲ የዜጎችን ሰቆቃ ለማንሳት ባይፈቅዱም የሳኡዲ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ህገወጥ ስደተኞች ተይዘው ወደ ሃገር ቤት እንዲባረሩ ፈርሟል ሲሉ የሳኡዲ ዲፕሎማቶች በበኩላቸው መንግስታችሁ የፈጠረው ክፍተት ነው በማለት ሁሉንም ለወያኔ መሪዎች አሸክመዋል።
#ምንሊክ ሣልሳዊ#
No comments:
Post a Comment