ዛሬ ከሰአት ከልምምድ መልስ ዋልያዉ አንድ ልዩ ዝግጅት ላይ ተገኝትዋል፤”እስማማለሁ አልስማማም” የሚባለዉ ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን አስመላሽ ቡድኑን ጋብዞ ነበር፤ከተጫዋቾቱ መሀል በዋልያዉ ምርጫ አዳነ ግርማ “እስማማለሁ አልስማማም” ጨዋታ ዉስጥ ገብትዋል፤
ለዋልያዉ ሲባል በዛሬዉ ቀረጻ የዉድድሩ ጣራ የሆነ ገንዘብ ተመደበ፤አዳነ እድለኛ ከሆነ 100ሺ ብር ተመደቦለታል፤100ሺዋን ቀደም ብሎ ጠራት፤ቀጥሎም ከፍተኞቹን እና እደለ ቢሶችን ቀላል ብሮች አለፋቸዉ፤የመጨረሻዉ ጥሪ ላይ ሁለት ሳጥኖች ቀሩ፤አንዱ ሳጥን 50ሺ ብር አንዱ ደግሞ 1500 ብር ብቻ ይዝዋል፤ባለ 50ሺዉን የያዘዉ ሳጥን 3 ቁጥር ነዉ፤ባለ 1500 ደግሞ 19 ቁጥር ነዉ፤
አዳነ ከሁለቱ አንዱን ሲመርጥ– የመረጠዉ ቁጥሩ የያዘዉን ብር ያገኛል፤ወይ 3ቁጥርን ወይ 19ኝን…ተጫዋቾቹ እና ተመልካቹ 3ቁጥርን ምረጥ ብለዉ ጮሁ..እሱ ግን 19ቁጥር የምለብሰዉ ማልያ ቁጥር..የልጄ ስም ገብርኤል…ቀኑም 19 ብሎ….. 19ኝን መረጠ፤50ሺ ብርዋ ግን 3ቁጥር ላይ ነበረች….አዳነ የታሰበዉን ያህል ባያገኝም ከጨዋታዉ 1500 ብር አግኘቶ ዉድድሩ አልቅዋል፤
ዉድድሩ በእድል ላይ የተመረኮዘ ነዉ፤እናም በዚህ ዉድድር ከፍተኛ ብር ማግኘት የቻሉት 2ት ሰዎች ብቻ ናቸዉ፤አንዱ የዋልያዉ ዋና አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ናቸዉ፤ከ15ሺ ብር በላይ አግኝተዋል፤የአዳነ እና ዋልያዉ የ”እስማማለሁ አልስማም” ፕሮግራም በኢቲቪ 3 ከመልሱ ጨዋታ በፊት እንሚቀርብ ይጠበቃል፤
ጥዋት ላይ በተደረገዉ ልምምድ አንድ ሰዉ አልሰራም፤ፋሲካ አስፋዉ ከክለብ አጋሩ ቶክ ጄምስ ሜዳ ላይ በተገባበት ሸርተቴ ጉዳት ደርሶበታል፤ቀለል ያለ ጉዳት ነዉ…እናም በጥቂት ቀናት ወደ ልምምድ እንደሚመለስ ተስፋ ተደርግዋል፤ከፊንላንድ የመጣዉ ፉአድ ኢብራሂም ዛሬ ከዋልያዉ ጋር 3ተኛ ልምምዱን አድርግዋል፤በመጀመሪያዉ ቀን አየሩ ከብዶት እንደነበር በቀጣይ ቀናት የተሻለ እንደሆነ ታይትዋል፤
ፕሮፌሽናሎቹን በተመለከተ የዋልያዉ ሰዎች ለየክለቦቹ ደብዳቤ ጽፈዋል፤እናም ከጨዋታዉ 7ቀናት ቀደም ብለዉ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተስፋ ተደርግዋል፤

No comments:
Post a Comment