Saturday, January 4, 2014

የምስካዬ ህዙናን መድሀኒያለም ገዳም ሰራተኞች አስተዳደሩን አማረሩ

በገዳሙ እንክብካቤ እንጂ ጭቆናና እንግልት የለም /የገዳሙ አስተዳደር/
የምስካየ ህዙናን መድሀኒያለም ገዳም ሰራተኞች በቤተ - ክርስቲያኑ አስተዳደር ከፍተኛ ጭቆናና በደል እንደሚደርስባቸው ተናገሩ፡፡ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መላዕከ ገነት አባተክልማርያም አምኜ የገዳሙን ሰራተኛየ ሚያስተዳድሩት እንደመፈንሳዊ አባት ሳይሆን እንደ አምባገነን መሪ ነው ሲሉ ሰራተኞቹ አማረዋል የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ አባ ተ/ማርያም አምኜ በበኩላቸው በቤተክርስቲያኒቱ ሁሉም ስርዓትና ደንብን ተከትሎ እንጂ ያለ አግባብ የሚንገላታም የሚጨቆንም የለም ሲሉ መልሰዋል፡፡ “ቤተክርስቲያኑ የሚመራው በፓትሪያርኩ ነው” ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ የደሞዝ ማነስን ተከትሎ እንዲያነጋግሩን አባ ተክለ ማርያምን ለስብሰባ ጠርተን እግረ መንገዳችንን የገዳሙን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ እርሳቸው ያለ አግባብ የሚሰሯቸውን ስራዎች፣ እና አጠቃላይ ያለውን ችግር አስረዳናቸው ይላሉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ፡፡

የኢንጂነር ጀሚል ሀሰን ጉዳዮች በድጋሚ ተፈረደባቸው

  •                                                                              Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
የሀዋሳ ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው  ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ.ም በእስልምና ሀይማኖት በየወህረ የሚከበረውን “ሊቃ” የተሰኘ ሀይማኖታዊ በዓል ለመካፈል ወደ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ሚኬኤሎ ገበሬ ማህበር መልካሜ መሰጊድ የሄዱትና በእነ አቶ ሰልማን ሰይድ ፋሪስና አጋሮቻቸው በድንጋይ ተቀጥቅጠው የሞቱት የኢ/ር ጀሚል ገዳዮች በደቡብ ክልል ሀዋሳ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በድጋሚ ተፈረደባቸው፡፡ የሀዋሳ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ታረቀኝ አበራም ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ የስንብት ደብዳቤ እንደደረሳቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ግንቦት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በአካባቢው “የሀይማኖት መሪ” እየተባለ የሚጠራው አቶ ሰልማን ሰይድ ፋሪስ ነገ ከአዲስ አበባ የሚመጡና የሊቃ በዓላችንን ሊያበላሹ የተዘጋጁ ሰዎች አሉ ሲመጡ በዱላ ደብድባችሁ ደሉ በሚል ባስተላለፈው ትዕዛዝ ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ.ም በበዓሉ ላይ የተገኙት ኢ/ር ጀሚል ሀሰን በድብደባው ህይወታቸው ሲያልፍ በበርካቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት:የቀድሞው ፕሬዚዳንት እና ሴት ልጃቸው በፍርድ ቤት ክስ ቀረበባቸው::


የ2.4 ሚሊየን ብር ካሳ ይከፈለኝ" የሚል ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ገብቷል::
ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አሁን የሚኖሩበትን ቤት አፈላልጎ ያከራያቸው ግለሰብ 360,000 ብር የአገልግሎት ክፍያ አልተከፈለኝም ሲል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን፣ ሴት ልጃቸውን መና ግርማ ጨምሮ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤትን ከስሷል፡፡

ከሳሹ የአገልግሎት ክፍያውን ከማን ማግኘት እንዳለበት እንዳላወቀና ፍርድ ቤት አጣርቶ እንዲያሳውቀውም ጠይቋል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት በበኩሉ ክፍያው የመንግስትን ጥቅም ስለሚጎዳና ክሱን ለመከራከርም ጽ/ቤቱ የህግ ባለሙያ ስለሌለው ፍትህ ሚንስትር ወክሎ እንዲከራከርለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፍትህ ሚንስትር ጽፏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም፣ ከዚህ በፊት ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቤት ለማከራየት ውል ተዋውዬ፣ ቤቴን አሳድሼና ሌሎችንም በርካታ ወጪዎችን አውጥቼ ውሉ ፈርሶብኛል ያሉት ግለሰብ በዚሁ ሳቢያ ለደረሰብኝ ጉዳት የ2.4 ሚሊየን ብር ካሳ ይከፈለኝ የሚል ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት አስገብቷል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ አስታውቋል፡፡

source:Minilik Salsawi

Letter of Complaint to DW from Oromo Students; RE: Defamatory and Discriminatory DW Amharic Program Against the Oromo People

The following is a letter of complaint to the Broadcasting Board of the (DW – popularly known as the ‘German Radio’) from the Union of Oromo Students in Europe-Germany (UOSG) regarding the DW Amharic Service’s defamatory and discriminatory program against the Oromo people. 

በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች

ኢሳት ቲቪ በዛሬ ስርጭቱ እንደዘገበው በሞያሌ ከተማ የኦነግ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ስትታመስ ዋለች። ባለፈው ረቡእ ታጣቂዎቹ ከቀኑ 10 ሰአት ገደማ ወደ ከተማዋ በመግባት 3 ጠባቂዎችን በመግደልና አንደኛውን ታጣቂ መሳሪያውን በመቀማትና ልብሱን በማስወለቅ ” ሂድና ለአለቆችህ ንገር” በማለት ጉዳት ሳያደርሱበት መልቀቃቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ አንድ ድግን መትረጊስ፣ አንድ ላውንቸርና አንድ ባዙቃ ማርከው ወስደዋል። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው የደረሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎችን እየደበደቡ ሲያሰቃዩ መቆየታቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አንድ ሹፌር ለኢሳት እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳፋሪዎችን ከመኪና ላይ በማስወረድ ድብደባ እንደፈጸሙባቸውና እርሳቸውም በጥፊ እንደተመቱ ተናግረዋል
“እኛ ለምን እንደተደበደብን አልገባንም” የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሁኔታው እስከትናንት ድረስ ውጥረት የነበረበት እንደነበርና ፍተሻው በእየጫካው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
ታጣቂዎቹ በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሳቸውም ተገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያ የሞያሌን አስተዳደር ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። መንግስትም በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።
ኦነግ ገዢውን ሀይል በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ከሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግስት ታጣቂዎች በኦጋዴን ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኦጋዴን ፕሬስ ዘግቧል።
ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሀይሎች ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በወሰዱት እርምጃ ፍሪህ ደሃግ አዳር የተባለው ሰው ሲገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።

አይ ስብሐት ነጋ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን “አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት…” …read more
Source: Ecadforum

Friday, January 3, 2014

ጄነራል ሳሞራ የኑስ የወጠኑት ሴራ የጄነራል አበባ ታደሰን ህልውና አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

ከተወሰኑት ወራት በፊት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ አዛዦች የሆኑት ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ ጄኔራል ሞላ ሃይለማርያምና ጄ/ል ሰአረ መኮንን ማእረጋቸው ሳይነካ ከተወሰኑ የሀላፊነት ቦታቸው ዝቅ ብለው እንዲሰሩ መወሰኑ የጦሩ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በሶስቱ ጎምቱ አዛዦች እና ውሳኔውን ባስተላለፉት በኢታማጆር ሹሙ በጄኔራል ሳሞራ የኑስ የተፈጠረው አለመግባባት መንስኤ ለብዙዎቹ ግልጽ አልነበረም። እነሆ ከወራት በሁዋላ ኢሳት የተወሰኑ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችን በማነጋገር ያጠናከረውን ሪፖርት ያቀርባል። የመረጃ ምንጮቻችን በኮሎኔልነት ማእረግ ደረጃ ያሉ ናቸው። ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እና ድምጻቸው እንዲካተት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ጊዜው ሲፈቅድ አዛዦቹ እራሳቸው ታሪኩን ይፋ እንደሚያወጡት ቃል በመግባታቸው እስከዛው በእነሱ በኩል ያለውን እይታ እንደሚከተለው እናቀርበዋልን።

Ethiopia – A Prison House for Oromo!

A list of innocent Oromo & other people in Ethiopian prisons who are sentenced to Death or Life imprisonment by Ethiopian government.
Tarree Hidhamtoota Siyaasaa Manneen Hidhaa Qaalittii, Qilinxoo, Maa’ikalaawii fi Zuwaayitti
hidhaman hanga tokko (2013)1466058_723389524355157_1880754403_n
Click below for the List of the Prisoners.

Thursday, January 2, 2014

ለአራት የፌዴራል ፖሊስ አባላት በግድያ ወንጀል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ ሰጠ።

በቂም በቀል ተነሳስተውና አስበው፤ አንድን ሰው በእንጨት ዱላ ደብደበው ገድለዋል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተባቸው አራት የፌዴራል
ፖሊስ አባላት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በ6 ዓመት ከ7 ወራት እና በ5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔ ሰጠ።

አንደኛ ተከሳሽ ምክትል ሳጅን ብሩክ ሽፈራው፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ኮንስታብል ኃይላይ አርአያ፣ ሶስተኛ ተከሳሽ ኮንስታብል ፀጋዬ ወ/አረጋይ እና አራተኛ ተከሳሽ ሆነው የቀረቡት ኮንስታብል ታዬ ጭንዲን የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ የመሰረተባቸው ክስ ሁለት ሲሆን፤ በ1ኛው ክስ ስር አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበው ዝርዝር፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሰውን ለመግደል አስበው ሰኔ 2 ቀን 2004 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6
ሰዓት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 09/14 ልዩ ቦታው ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ጨካኝነታቸውን በሚያሳይ ሁኔታ 1ኛ ተከሳሽ ምክትል ሳጅን ብሩክ ሽፈራው ሟች ሃሚድ ወዳጆን በእንጨት ዱላ ጭንቅላቱን እና ጀርባውን ደጋግሞ ሲመታው፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችም የሟችን ጭንቅላት በዱላ በመምታት ጉዳት እንዲደርስበት ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ራሱን በመከላከል በማይችልበት ሁኔታ በመግደላቸው በፈፀሙት ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከሰዋል ይላል።

መንግስት አሁንም ሀይሉን አጠናክሮ በሙስሊሙ ላይ ሌላ አዲስ ዘመቻ ሊከፍት እንደሆነ የፍትህ ሬዲዩ ምንጮች አስታወቁ፡፡

መንግስት አሁንም ሀይሉን አጠናክሮ በሙስሊሙ ላይ ሌላ አዲስ ዘመቻ ሊከፍት እንደሆነ የፍትህ ሬዲዩ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ለሶስት ቀን የሚቆይ ስልጠና ከትናንት ጀመሮ በሚኒስትር መ/ቤት ደረጃ መጀመሩ ተገለፇል ::
ከባለፈዉ ሶስት ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች በሚገኙ የሚገኙ የክፍለ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ፣ አ.አ ፀጥታ ቢሮ፤ የአ.አ ፍትህ ቢሮ እና የአ.አ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በእስልምናና በሙስሊሙ ላይ አዲስ ዘመቻ ሊከፍቱ እንደሆነ ታውቋል ፡፡ ይህን በማስመልከትም በከፍተኛ የኢሃዴግ አመራሮች አማካኝነት በስልጠና መልክ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ተመልክቷል ፡፡ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለማወቅ እንደተቻለው ስልጠናው እንደ ዋና አላማ አድርጎ የተነሳው የተጀመረው የመስጂድ ነጠቃ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታና እስከዛሬ በተደረገው የመስጂድ ንጥቂያ የተገኙ ውጤቶችን መገምገም ፣ መስጂድ ነጠቃውንም ሆነ ሌሎች መንግስታዊ እርምጃዎችን ተከትሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከዚህ በኋላ ለሚያሰማው ህዝባዊ ቁጣ የመንግስት ሃላፊዎች ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው አቅጣጫ የሚያመለክቱ እንሆነ ታውቋል ፡፡