Friday, October 4, 2013

ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው


መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ 2005 የስራ አፈጻጸምና 2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል።
በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ የነበረው ስብሰባም እንዲሁ በተመሳሳይ ተቃውሞ መጠናቀቁን በውይይቱ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ በርካታ አጀንዳዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጉዳዮች ተሰብሰባዊውን በከፍተኛ ሁኔታ አወዛግበዋል።
2006 ዓም የጸረ ሰላም ወይም የጥፋት ሀይሎችን ማምከን የሚል በእቅድ እንዲካተት በቀረበው አጀንዳ ላይ ጸረ ሰላም ማን ነው የሚለው ጥያቄ በተሰብሳቢው ተነስቶ የመድረኩ መሪዎች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል። የዞኑ የጸጥታ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ /ማርያምነሀሴ ወር ገደማ 30 የሚሆኑ ሰዎች በጎንደር ከተማ ህዝቡን ተነስ በማለት ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሰዎች ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው።በማለት አንድነት ፓርቲ በጎንደር ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምሳሌነት አንስተዋል።
ሌላው የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ገዛሀን ተክሌ በበኩላቸውየኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጠ ብሎ መናገር ጸረ ሰላምነት ነውሲሉ አብረራርተዋል። ባለስልጣኑ አክለውም ህገመንግስቱን ለመጣስ የሚነሳ ሁሉ ጸረሰላም ተብሎ ይፈረጃል ብለዋል።
የጸጥታ ጉዳዮች ዘርፍ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ደግሞከመድረክ አፈንግጦ መውጣትና ሳያስፈቅዱ መናገር፣ ሳያስፈቅዱ ጽሁፍ መጻፍና ማሰራጨት፣ ሳያስፈቅዱ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ በጥፋት መልእክተኝነት ያስፈርጃል ሲል ገልጸዋል።
አቶ ፈንታ የተባሉ ባለስልጣንም እንዲሁየጎንደርን መሬት ኢህአዴግ አሳልፎ እየሰጠ ነውብሎ መናገር ጸረ-ሰላም ተግባር ነው በማለት የራሳቸውን ትርጉም አቅርበዋል።
ስለ ጸረ ሰላም ሀይሎች፣ አክራሪነትና ሽብረተኝነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ትምህርት እንዲሰጠጥ በቀረበው ሀሳብ ላይ ደግሞ በስብሰባው የተሳተፉ ተቃውሞአቸውን ገልዋል። ተሳታፊዎቹ 15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ስለ ሽብረተኝነት፣ አክራሪነትና ጸረሰላም ሀይሎች ማስተማር በህጻናቱ ላይ የስነልቦና ጫና ይፈጥራል በማለት ተከራክረዋል።
ሌላው አወዛጋቢ የነበረው ነጥብኢህአዴግ 2006 እቅድን ተቋሞችን በድርጅት አባላት በመሙላት እናሳካለን በማለት ያቀረበውሲሆን፣ ተሰብሳቢዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሁሉ በድርጅት አባላት ከሞላችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን ምን ልታደርጉዋቸው ነው?” በማለት ጥያቄ አንስተዋል።
ለሱዳን ተላልፎ የተሰጠውን መሬት በተመለከተ የአካባቢው ሰራተኞች የሁለቱን አገሮች ድንበሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆኑ በኢህአዴግ የቀረበውን ማስጠንቀቂያ አልተቀበሉትም።

ወያኔ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ስራ መጠመዱ ተሰማ፤


ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚወስዱ አዉራ መንገዶች ታንኮችን፤ መድፎችንና ሌሎችም ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በተሸከሙ ከባድ ወታደራዊ የጭነት ማመላለሻ ከሚዮኖች እየተጨናነቁ መሆኑን ኢሳት ቴሌቪዥንና ሬድዮ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘገበ። ወያኔ ከኤርትራ ጋር ባለበት የድንበር አተካሮ ብዙም
ዉጥረት በማይታይታይበት በአሁኑ ወቅት የጦር መሳሪያዎቹን በዚህ ደረጃ ለማንቀሳቀስ ለምን እንዳስፈለገ ብዙም የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አንዳንዶች ወይኔ ሀይሉን ለማሳየት የሚያደርገዉ ከንቱ የእዩኝ እዩኝ ዘመቻ ነዉ ሲሉ ሌሎች ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን እያየለ የሚጣዉን የአማጽያን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነዉ ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴዉን አስመልክቶ ከአገዛዙ ባለስልጣናት የተሰጠ መግለጫ ካለመኖሩም በላይ ሦስተኛ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ከመንግስት ጋር ያደረጉት
ግንኙነትም ፍሬ አልባ ሆኗል። ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ፤ ጎንደርና አፋር ዉስጥ የወያኔን ስርዐት በኃይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱ አያሌ መሳሪያ ያነገቡ ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ላለፉት ሃያ አመታት በተናጠል ወያኔን የተዋጉ ኃይሎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጋራ ግንባር እየፈጠሩ መምጣታቸዉ ወያኔን እንዳሳሰበዉና ክፉኛ
እንዳስደነገጠዉም ታዉቋል።

እንደብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ግምት ይህ ከሰሞኑ የታየዉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴም የዚሁ ድንጋጤ ዉጤት ነዉ የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ የነጻነት ኃይሎችን ለመቀላለቀል የሚደረገዉ እንቅስቃሴ እያደገ መምጣቱ ሌላዉ የወያኔ ስጋት ስለሆነ የሰሞኑ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገዉ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከመሀል የአገሪቱ
ክፍሎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችንና ኬላዎችን ለመዝጋት ነዉ የሚሉም አልታጡም። በዚህ ተኬደ በዚያ የሰሞኑ የወያኔ ወታደራዊ ሩጫ አላማዉ
ባዕዳንን ለመከላከል ሳይሆን ለአገር አንድነትና ለህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎችን ለማፈን ነዉ።

ከሰብአዊ

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ከነበሩት ተመስገን ስዩም ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ሲያዝ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዶዘር ደግሞ ማሳገዱን የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለፀ፡፡
የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአቶ ተመስገን ስዩም ላይ ያካሄደው ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት 12 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎችን በሌላ ሰው ስም ገዝተው ለተገዙት መኪኖች ውክልና በመውሰድ መኪኖቹን ለሌሎች ሰዎች ሸጠዋል፡፡
ከሽያጩ በተገኘው ገንዘብ ደግሞ ሁለት ዶዘሮችን ለመግዛት ከ15 ሚሊዩን ብር በላይ ለአንድ ድርጅት ክፍያ ፈፅመዋል፡፡
ግለሰቡ ክፍያ ከፈፀሙባቸው ዶዘሮች መካከል አንዱን በ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በመረከብ ለአንድ ድርጅት ያከራዩ ሲሆን ሌላውን 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣውን ዶዘር ለመረከብ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ግለሰቡ ይህን ያደረጉት ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በመያዝ ከሚመጣ ተጠያቂነት ለማምለጥ እና በሙስና የተገኘን ህጋዊ አስመስሎ ለማቅረብ እንደሆነ በጉዳዩ ዙሪያ እስካውን የተደረገው ምርመራ ያመላክታል፡፡
እነዚህን የተጠቀሱትን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ በማስመሰል ሂደት ተሳትፎ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ነጋዴዎች ከ14 ቀን በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፥ ነጋዴዎቹ አቶ ተመስገን ስዩምን ለመርዳት የፈለጉት ቀደም ሲል ግለሰቡ በሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት ነጋዴዎቹ በህገ ወጥ መንገድ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ ይጠቅሟቸው ስለነበር እንደሆነ ምርመራው ያስረዳል፡፡
በመሆኑም ገንዘቡና ንብረቱን ከሙስና ጋር የተያያዘ ነው በሚል ጥርጣሬ ግለሰቡ አንድ ዶዘር የገዙበት 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ከተገዛበት ድርጅት እንዲመለስ ተደርጎ ኮሚሽኑ የተረከበው ሲሆን ፥ ሌላው 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው ዶዘር እንዲታገድ ተደርጓል ፡፡
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ስዩም ባለፈው ሰኔ በርካታ የገቢዎችና ጉምሩክ የስራ ሃላፊዎች ፣ ነጋዴዎችና ትራንዚተሮች በሙስና ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ሲፈለጉ ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በመሸሽ ደቡብ ሱዳን ለመግባት ሲሉ መያዛቸው ኢሬቴድ በዘገባው አስታውሷል ።      

ለፈውስ ያልነው ለሞት!(መታሰቢያ ካሣዬ)

ለፈውስ ያልነው ለሞት!
እነፓራሲታሞል ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ
እንደ አለም ጤና ድርጅት ትርጓሜ፤ መድሃኒቶች በርካታ ንጥረ ነገሮችን የያዙ በሽታን ለማከም የሚረዱና ለህመምተኞች በሚስማማ መልኩ ተዘጋጅተው በፋብሪካ ደረጃ እየተመረቱ ገበያ ላይ የሚውሉና በጤና አገልግሎት ውስጥ ወሳኝ ሚና ያላቸው ኬሚካሎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች በተገቢው ጊዜና ሁኔታ፣ በትክክለኛው መጠንና በባለሙያ ትዕዛዝ ሲወሰዱ የታለመላቸውን ግብ በመምታት በሽታን ለመከላከል፣ለማከምና ህመምተኛውን ወደ ጤናማ ሁኔታ ለመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው መድሃኒቶች በዘፈቀደና ያለባለሙያ ትዕዛዝ አሊያም ከታዘዘው መጠን በላይ ወይም በታች ሲወሰዱ ፈውስነታቸው ቀርቶ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ መርዞች ሊሆኑብን ይችላሉ፡፡ መድሃኒቶች ነፍስን የመታደጋቸውን ያህል ህይወትን ሊቀጥፉ ይችላሉ፡፡ ለህመም ማከሚያና ማዳኛ የሚወሰዱ መድሃኒቶች ፈዋሽ ናቸው የሚባሉት የታለመላቸውን ግብ በአግባቡ መምታት ሲችሉ ነው፡፡

ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አፈጻጸም ላይ ድክመት ማምጣቱን በመገምገም የማሻሻያ እርምጃ መወሰዱን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ አቶ ደመቀ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉትና ትላንትናና ዛሬ ታትሞ በወጣው ቃለምልልሳቸው ላይ አቶ መለስ ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አንዳንድ ዘርፎችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሸ ችግር እንዳጋጠመ አምነዋል፡፡ “ባለፉት ዓመታት ሥራዎቻችንን ስንገመግም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብዙ ስራ ተሸክመው ይሰሩ በነበረበት ወቅት ዋና ዋና የልማት ስራዎች ላይ በማተኮር አንዳንድ የሚኒስቴር መ/ቤቶችና የልማት መስኮች በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሽ በዝርዝር ዕቅድ ግምገማና ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተቶች እንደነበሩ እንደ ችግር በጋራ ያገኘናቸው ነጥቦች አሉ”፡፡ ብለዋል ምክትል ጠ.ሚኒስትሩ ጋዜጣው ከአቶ መለስ ሕልፈት በኋላ በተካሄደው የስልጣን ሽግሽግ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ የክላስተር አስተባባሪዎች መሾማቸው በአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች መካከል ያለውን አለመተማመን የሚያሳይና ምክትል ጠ/ሚኒስትርነቱን ስልጣን ለሁሉም ለማዳረስ የተደረገ ነው ስለመባሉ ጥያቄ ቅርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “አቶ መለስ ታግሎ የሚያታግል ጠንካራ መሪ ነው፡፡እሱን ማጣት ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ጉድለቱን ዝም ተብሎ እዚያና እዚህ በዘመቻ የሚሞላ አይደለም” ሲሉ የተናገሩት አቶ ደመቀ፣ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ አንድ ሰው በቀጥታ አቶ መለስን ባይተካም የጋራ አሰራርን በማጠናከር የተለያዩ የስራ ክፍፍሎች በማድረግ የጋራ አቅም አጎልብቶ እንዴት የህዳሴውን ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል ይቻላል የሚለው በስፋት የተመከረበት ጉዳይ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም በሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ በመሰየም የተለያዩ ክላስተሮችን እንዲያስተባብሩ ማድረግ ያለመተማመን መገለጫ አይደለም በማለት ወቀሳውን አስተባብለዋል፡፡ እነዚህን ችግሮች በመፍታት ድጋፍ ለማድረግ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ የክላስተር አደረጃጀት ማስፈለጉን የጠቀሱት አቶ ደመቀ የበለጠ አቅም ለማሳደግ፣የተሟላ የመሸከም ብርታት ለመስጠት ይህ የጋራ አሰራር መተግበሩን አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውጥረት ነግሷል፡፡ (Minilik Salsawi)

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውጥረት ነግሷል
በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 5ኪሎ ግቢ(institution of technology) ተማሪዎች ከ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ እንዳይወጡ መከልከላቸው ታወቀ፡፡


በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 5ኪሎ ግቢ(institution of technology) ተማሪዎችን በአክራሪነት እና ጽንፈኝነት ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በማቀድ የግቢውን ተማሪዎች ለመስብሰብ ሙከራ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች የገለጹ ገልጸዋል::

ሆኖም ግን በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ተማሪዎች በአክራሪነት ዙሪያ እንደማይወያዩ እና ሙስሊም ተማሪዎቹ የጁምአ ሰላት ስግደት ስላለባቸው ለመውጣት ቢሞክሩም የግቢውን ቅጥር ግቢ በመዝጋት ወደ ስብሰባው ቦታ በግደጅ ለማስኬድ መኪና ውስጥ እያስገቧቸው እንደደሆነ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡

Ethiopian Hydropower Dam Assessment Warns of Structural Weakness

a-dam-on-the-river-nile
By William Davison
(Bloomberg News) – Ethiopia’s plan to build Africa’s biggest hydropower dam on the main tributary of the Nile River must address concerns that there may be flaws in the design of its foundations, a group of international experts said.
They also called for further studies on what impact the 6,000-megawatt, $4.7 billion project may have on the downstream nations of Sudan and Egypt, the International Panel of Experts said in a report e-mailed to Bloomberg News and verified by Ethiopia’s Foreign Ministry. Egypt, which relies on the Nile for almost all of its water, expressed alarm about the dam when Ethiopia in May diverted the Blue Nile as part of the construction process.
“Structural measures might be needed to stabilize the foundation to achieve the required safety against sliding” of the main dam, according to the report. There are also “weak zones” in the rock that will support an auxiliary dam that need to be studied, it said.
Construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam is part of a government plan to spend 569 billion birr ($30 billion) on infrastructure in the five years through mid-2015. The country, Africa’s second-most populous nation, targets becoming an industrialized middle-income nation by 2025.
Ethiopia is the source of 86 percent of the water that flows into the Nile, the world’s longest river that runs 4,160 miles through 11 countries from Burundi in the south to Egypt, where it empties into the Mediterranean Sea. Ethiopia has said it will take five to six years to fill the 74 billion cubic-meter (2.6 trillion cubic-feet) reservoir created by the dam.
Regional Specialists
The panel, which held its first meeting in May last year, was formed at the suggestion of Ethiopia’s government. It comprised two specialists each from Ethiopia, Egypt and Sudan and four from other nations. The report, which hasn’t …read more

Thursday, October 3, 2013

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በግድ ዩኒቨርሲቲው እንዲለቁ ተደረገ


(ዘ-ሐበሻ) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የሳይንስና ቴክኖሊጂ ተማሪዎች አስተዳደሩ COC (ፈተና) እንዲወስዱ በማስገደዱና ተማሪዎቹም ካለምንም ዝግጅት አንፈተንም፤ ጊዜ ሊሰጠን ይገባን በሚል ያነሱት አለመግባባት እየተካረረ ሄዶ ተማሪዎቹ በግድ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።
ተማሪዎቹ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ፈተና ድንገት መውሰድ የለብንም ከተማሪዎቹ መካከልም 30 በመቶ የሚሆኑት ውጤት በማጣት ከትምህርት ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ በሚል ስጋት ለማጥናት ጊዜ ይሰጠን ቢሉም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ምሳ እንደከለከልና ትናንት ጠዋትም ቁርስ ከከለከለ በኋላ አለመግባባቱ ተካሮ በመሄድ ማምሻውን ደግሞ ማደሪያም በመከልከሉ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ካለምንም ህጋዊ ማስታወቂያ በአስተዳደሩ ሳቢያ በግድ ከዩኒቨርሲቲው ከወጡ በኋላ በአካባቢው ባሉ ቤተክርስቲያኖች፣ ሆቴሎችና በየሰው ቦታ እንደተጠጉ ተገልጿል።
ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ትዘግባለች።

Arbaminch University Students have been forced to leave the campus

By Hagere Ethiopia
Arbaminch University Students have been forced to leave the campus after depriving them of food & shelter. According to one students statement, there had been a serious disagreement with the university’s management who was forcing them to take the Holistic Examination immediately. Students argued that if this should take place, then we should have been told earlier so that we have plenty of time to be prepared. And that it is totally unfair and cruel to force them to take it at the 11th hour (at the year of their graduation). After calling this students who according to the management should take the examination, the board decided to stop both the cafeteria & dormitory services. And as of now they have been forced to leave the campus by the use of police force. All of them with no exception to girls & the ill are all scattered in the city churches, hotels,…. And some are already heading back to their homes.

Ethiopia the only nation in Africa which filters the Internet

Freedom House
October 3, 2013

SEATTLE - Ethiopia is the only nation in Africa that uses Internet filtering, though the country has 1% internet penetration, the lowest in the world for a population of 87 million, says a new study by Freedom House. "Despite low access, the government maintains a strict system of controls over digital media, making Ethiopia the only country in Sub-Saharan Africa to implement nationwide internet filtering. Such a system is made possible by the state’s monopoly over the country’s only telecom company, Ethio Telecom," according to the new report. Details follow: