ለምን?
አሜሪካ የሚኖር “አርቲስት” ነው። ራሰ በረሃና እድሜው በ40ዎቹ መጨረሻ የሚገመት ነው። ብዙዎች በፊልም ስራው ያውቁታል። ይህ ሃበሻ የብዙ ሴት እህቶቻችንን ህይወት እያበላሸ የሚገኝና የአውሬ ተግባር እየፈፀመ የሚገኝ “ሰው” ተብዬ ነው። በእድሜ ሊወልዳቸውና የልጅ ልጆቹ ሊሆኑ የሚችሉ ወጣት ልጃገረድ ሃበሻዎችን በማጥመድ በህይወታቸው ላይ ሞት እየፈረደ ነው። ስሟን እንድደብቅላት አደራ ያለችኝ ሃበሻ ወገኔ እንዲህ አለችኝ፥ «..ይህ “ሰው” በአርቲስትነቱ ሽፋን አድርጐ ቀረበኝ። ፊልም አሰራሻለሁ አለኝ። ..ከዚያም አንሶላ እንድንጋፈፍ አድረገ። አብሬው ከተኛሁ በኋላ ስለእርሱ ማንነት (ያለበትን በሽታ) ሰዎች ነገሩኝ። ማመን አቃተኝ። ሆስፒታል ሄጄ ተመረመርኩ። የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቫይረስ እንዳለብኝ ተነገረኝ። ፍርድ ቤት ሄጄ እንዳልከሰው- ማንነቴ በሚዲያ ከወጣ በማኅበረሰቡ ልገለል እችላለሁ ብዬ መተውን መረጥኩ። ..ሌላው ቀርቶ ለቤተሰቤ እንኳ ብናገር አይቀበሉኝም። ልክ ነኝ አይደል?…እንኳን ቤተሰቤ አንተ ትቀበለኛለህ?…(እንባ እየተናነቃት) ..ግን ይህ ነውረኛ የሌሎች ሴት እህቶቼን ህይወት እንዳያበላሽ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። ከዲሲ ውጭ ያሉና ስለርሱ ማንነት የማያውቁ ሴት ወጣት እህቶቼን በተለያየ መንገድ እያጠመደ ቫይረሱን ያስተላልፋል። ግን ለምን?…ህይወቴን አጨለመው። ምን እንደምል አላውቅም….ግን ለምን!?…ምን አይነት አውሬነት ነው?…» በልቅሶ የታጀበና እጅግ ምሬት የተቀላቀለበት ጥያቄዋ ነበር። …ይህ “ሰው” ወይም አርቲስት ተብዬ ይህን ነውረኛ ድርጊቱን ገፍቶበታል። ..ግን ለምን!?…
አርአያ ተስፋማሪያም
No comments:
Post a Comment