(ዘ-ሐበሻ) የአሜሪካ መንግስት የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ወደ ሃገሩ ገብተው እንዲኖሩና እንዲሰሩ የሚፈቅድበት የዲቪ ሎተሪ ከመስከረም 21 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2007 ዓ፣ም መሞላት እንደሚጀምር ዘ-ሐበሻ ከስቴት ዲፓርትመንት ያገኘችው መረጃ አመለከተ።

ምናልባት የኢንተርኔት መስመር መጨናነቅ ስለሚኖር አመልካቾች እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ መጠበቅ የለባቸውም ያለው የስቴት ዲፓርትመንቱ ማሳሰቢያ በእድሉ መጠቀም የሚፈልግ ካለ በጊዜ ማመልከቻውን መሙላት አለበት ብሏል።
ምናልባት የኢንተርኔት መስመር መጨናነቅ ስለሚኖር አመልካቾች እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ መጠበቅ የለባቸውም ያለው የስቴት ዲፓርትመንቱ ማሳሰቢያ በእድሉ መጠቀም የሚፈልግ ካለ በጊዜ ማመልከቻውን መሙላት አለበት ብሏል።
ባንግላዲሽ፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ኮሎምቢያ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ኢኳዶር፣ ኤልሳልቫዶር፣ ሃይቲ፣ ሕንድ፣ ጃማይካ፣ ሜክሲኮ፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ፔሩ፣ ፊሊፒንስ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኢንግላንድ (ከሰሜን አየርላድ ውጭ)ና ቬትናም ባለፉት 5 ዓመታት ከ50 ሺህ ላይ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ስለገቡ የዲቪ 2016 ባለ ዕድል ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ስቴት ዲፓርትመት አስታውቋል። ይህም ማለት ኢትዮጵያውያን ይህን ሎተሪ መሙላት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የዲቪ ፎርም እንደሚሞላ በየከተማው በተለጠፉ ማስታወቂያዎችና በሚዲያ ላይ እያስተዋወቀ ይገኛል።