Thursday, October 3, 2013

ጥያቄው ሃይማኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ …

ይድነቃቸው ከበደ
የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሀላፊ
‹‹ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ ›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡
‹‹ መንኛው ሰው የመሰብ፤የሕሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው ፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይመኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣የመተግበር ፣የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡››ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 1 ፡፡
‹‹ ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ ማስገደድ ወይም መከልከል አይቻልም፡፡ ›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 3 ፡፡
የሙስሊሞች ጥያቄ
1ኛ. በስልጣን ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ያለምርጫ የመጡና ህዝቡን የማይወክሉ በመሆናቸው ህዝቡ በነፃ ፍላጎቱ፤ በገለልተኛ አስመራጮች እና በመስጂድ ደረጃ በሚመርጡ አመራሮች ይተኩልን፡፡
2ኛ. አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም ፡፡
3ኛ. አወሊያ የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የሌለበት ሲሆን ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር ፡፡
እነዚህን ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ደግሞ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በራሱ ፍቃድ 17 አባላት ያላቸውን ተወካዮች (ከሃገር ሽማግሌዎች፤ ከሃይማኖት ኣዋቂዎች፤ ከምሁራን እና ከሰባኪያን) ጥቆማውን በመቀበል እና ከመላ ሃገሪቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተፈረሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የድጋፍ ፊርማዎችን በማስረጃነት በመያዝ እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች ብቻ በመያዝ ምላሽ ለማፈላለግ ከላይ ታች ሲሉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሜቴዎች ስምንት ወራት አለፉ፡፡ በሂደቱ ከክፍለ ከተማ እስከ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ድረስ እነዚህን ጥያቄዎች በመተንተን በተለያየ ግዜ አቅርበዋል ውጤቱ ግን አራተኛ ጥያቄ ወለደ እሱም፡-
4ኛ. ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣታቸው ለእስር የተዳረጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሜቴዎች ይፈቱ ፤የሚል ነው፡፡
ሆኖም በምድር ላይ የሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ ፖለቲካዊ እንድምታ አላቸው ከሚል የተቆነጠረ ሃሳብ በመነሳት ምክንያቲዊ እና ወቅታዊ ነገሮችን ግምት ውስጥ ሳያስገብ ተቃራኒን ሃሳብ ለማሸነፍ ወይም ድጋፍ ለማግኘት ተብሎ መሰረታዊ የህግ ስእተት እና ፖለቲካዊ ወለምታ ከመዳረግ በፊት በመግቢያነት የተጠቀሱት የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎችና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ጎን ለጎን በማስተያየት የተሻለ ሃሳብ እስኪገኝ ድረስ ለድምዳሜ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተገለጹት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ የመብት ጥያቄዎች ናቸው መብት ደግሞ ከህግ የሚመነጭ ሲሆን የህግ ጥያቄ መጠየቅ በራሱ ፖለቲካዊ ጥያቄ መሆን አይችልም፤የፖለቲካ ጥያቄ መሆን የሚችለው እስላማዊ መንግስት እናቋቁም ወይም ፖለቲካዊ ሥልጣን ይኑረን እና የመሳሰሉት ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የተነሱ ሃሳቦች እና በዚህ ምክንያት የደረሰ ጉዳትና እስራት ቢኖር ሂደቱ ፖለቲካዊ ነው ብሎ በመደምድም በጉዳዩ ላይ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት አቋም መያዝ ይቻላል ግን እውነታው የመብት እንጂ ፖለቲካዊ ጥያቄ አለመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪ እነዚህ ግልፅ የመብት ጥያቄዎች በሃይል በመጠምዘዝ ፖለቲካዊ ይዘት ለማላበስ በመንግስት የሚደረገው ጥረት ለማንም ግልፅ ቢሆንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ንፁህ የመብት ጥያቄ ነው፤የፖለቲካ ጥያቄ ነው ለማስባል ተራ አሉባልታ ለማጠናከር ተደጋጋሚ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ዘጋቢ ፊልም በኢቲቪ በማቅረብ ያልተሳካ ጥረት ተደርጓል፤ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ የህዝብን አንድነትን ሊንዱ በሚችሉ መልኩ ተቀነባብሮ ሊቀርቡ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡
ይሁን እንጂ ከሃይማኖታዊ መቻቻል ባለፍ ሃይማኖታዊ መከባበር ላይ የተመሠረተ ግንኝነትን ባዳበር ህዝብ መካከል አንዳችም አስፈሪ ነገር እንደማይኖር ይገመታል፤ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው የሙስሊሙ ማህበረስብ ጥያቄ ከእምነት ነፃነት መብት የመነጨ ጥያቄ መሆኑን በመረዳት የሌላ እምነት ተከታይ ለሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያለሆነ ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል ይህ ደግሞ የመንግስትን አፍራሽ ተልኮ ያጋለጠ ነው፡፡
በመሆኑም የሙስሊሞች ጥያቄ ከህገ መንግስቱ ጋራ ሲመሳከር ሙሉ በሙሉ የመብት ጥያቄ ነው ለዚህም ነው ከአንድ ዓመት ከ 6 ወር በላይ ‹‹ ፍትህ ፍትህ ፍትህ ፍትህ………. ›› ሲሉ የከረሙት መንግስት ደግሞ በተቃሪኒው ‹‹ የሃይማኖት አክራሪነት ለማስፋፋት እና ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚጥሩ ›› በማለት እየወነጀላቸው ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሙስሊሞች ጥያቄ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ነው ፡፡
ስለሆነም የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ እና የመንግስት ተሳትፎ በማስተያየት ጥያቄው ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ላለመሆኑ እነዚህን ማስረጃዎችን መመልከት ተገቢ ናቸው፡-

1ኛ. መንግስት በቀጥታ እጁን በማስገባ የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ እና በመንግስት ካድሪዎች እንዲካሄድ አድርጓል፡፡የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ደግሞ የመጅሊስ ምርጫ በተቻለ ፍጥነት እና በገለልተኛ አስመራጭ አማካኝነት ምርጫ መካሄድ የሚኖርበት ሲሆን ጉዳዩም ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ባለመሆኑ በመስጂድ ሊካሄድ ይገባዋል፡፡
2ኛ. አህባሽ የተባለው እምነት ሸኽ አብደላ አልሃረሪ በሚባሉ የሚመራ እምነት በመንግስት ልዩ ድጋፍ ተደርጎለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በወኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አማካኝነት ሃምሌ 2003 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹ይህንን አመለካከት በሃገራችን ለማስፋፋት እንዴት ብንሰራ ይሻላል በሚል መንግስት ለረጅም ግዜ ሲመክር ቆይቷል›› በማለት በሰጡት ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ የአህባሽ እምነት ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከመኖሩ ባለፈም አስተምህሮቱን መንግስት ለማስፋፋት ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ደግሞ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡ የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ተጥሷል በተጨማሪ አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም ፡፡
3ኛ. አስተዳደራዊ የሆነ ጥያቄ ሲሆን እሱም አወሊያ ት/ት የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የለበትም ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚለው የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ነው ፡፡ ይህን ጥያቄ በሁለት መንገድ ማየት ይቻላል አንድም መጅሊሱ የሙስሊሙ ማህበረስብ ውክልና እንደሌለው ሁለተኛ ደግሞ የአወሊያ ት/ት አስተዳደር ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ካስፈለገ የተለያዩ መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚል ነው፡፡
4ኛ. ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮችን ለመግለፅ እና ለችግሮቹሁ መፍትሔ ለማፈላለግ የተመረጡ የኮሜቴ አባላት ከመንግስት ተወካዬች ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት ጥያቄው ሃይማኖታዊ መሆኑ እና መፍትሔም ሊገኝለት የሚችለው ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ ብቻ መሆኑን ሲያስረዱ ሰንብተዋል፤ መንግስትም በጉዳዩ ላይ ከኮሜቴ አባላት ጋር ሲደራደር ቆይቷል፡፡ይሁን እንጂ መንግስት በስተመጨረሻ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ተልካሻ አስተሳሰብ በመነሳት የኮሜቴ አባላትን በሽብርተኝነት ስም ከሶ ለእስር ዳረጋቸው፡፡
ይሁን እንጂ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ሲመረመር በየትኛውም መመዘኛ የሃይመኖት ነፃነት መብት ጥያቄ ነው ፤ በመንግስት በኩል ደግሞ እየሆነ ያለው ፖለቲካዊ አካሄድ ነው ለዚህም ነው ጥያቄችን ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም በማለት ከመናገር እና ከመፃፍ ባለፈም ሰላማዊ በሆነ መንግድ በተለያ ቦታና ጊዜ ድምፃቸውን ሲያሰሙ የከረሙት፡፡ የነገሩ አካሄድ እንዲ በሆነበት ሁኔታ የሙስሊሞች ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው በማለት ከፖለቲካ ፓርቲ መገለጹ ከስእተትም በላይ ስእተት ነው፤ ነገ ደግሞ ከችግሩ ለመላቀቅ በአቻነት አብረን እንስራ ወደሚል ጥያቄ እንዳያመራ ያሰጋል ፡፡ ነግር ግን በህገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች እንዲከበሩ አደርጋለው ለዚህም ድጋፋቹሁን ስጡኝ ብሎ የፖለቲካ አጀንዳ አድርጎ መታገል እና ጥያቄ ማቅረብ ከፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅ ተግባር ነው ፡፡

ተስፋዬ ገብረአብ በመጨረሻ እጅ ሰጠ

ተስፋዬ ገብረአብ እጅ ሰጠ
ከአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል
Tesfaye
Tesfaye Gebreab
ተስፋዬ ገብረአብ ከኤርትራዊያን ቤተሰቦች ቢሾፍቱ ተወልዶ ያደገ በውብ የስነጽሁፍ ችሎታው ብዙዎች የሚያደንቁት ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የ‹‹ብዙ ማንነቶች›› ባለቤት ነው፡፡ አዎ! ከሁለት ወር በላይ ባልዘለቀ የብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ መማረኩ በፈጠረለት ምቹ አጋጣሚ ከከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጋር ለመተዋወቅ ብሎም በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል መጀመሪያ ላይ ሆኖ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት የታጨ፤ በለጋ እድሜው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ የሆነለት የኢህአዴግ ሹመኛም ነበር፡፡ ያ ግን ትናንትና ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በማራኪ የስነጽሁፍ ችሎታው በልዩነታችን ውስጥ ስላለው ውበት ሳይሆን በልዩነታችን ልክ እንዴት መጥፋት እንዳለብን የሚሰብክ መሰሪ ባህታዊ ነው የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ ባህሪው ብዙዎች ግራ ተጋብተዋል፡፡ በተለይ የኤርትራ ገዢዎችን ስውር ዓላማ የሆነውን በኢትዮጵያ ላይ የዘር ጥላቻ የመንዛት ሰይጣናዊ ተልእኮ በየአጋጣሚው በስነ ጽሁፎቹ ላይ የማንጸባረቅ አመሉን የተረዱ ‹‹ተስፋዬ ገብረእባብ›› የሚል ስያሜ እስከመስጠት ደርሰዋል፡፡ እሱም ለኢትዮጵያ ያለውን ‹‹ተቆርቋሪነት›› ያለመታከት ይደሰኩራል፡፡
ዛሬ ግን ይህ ሰው እጅ ሰጥቷል፡፡ ለበርካታ ዘመናት የዘለቀው የተስፋዬ ብልጣብልጥነት በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ተጋልጧል፡፡ ለሁለት አመት ያህል ተስፋዬን በቤቱ አስጠግቶ ይህንን አስደናቂ የቤት ስራ የሰራው ወጣት አክቲቪስት አለማየሁ መሰለ ይባላል፡፡
Alemayehu Mesele
Alemayehu Mesele
ኢ-ፍትሀዊነትን በመቃወም፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚቃጣን አደጋ በመፋለም የሚታወቀውና፤ በእስር ብዛት አገሩን ለቆ እስኪሰደድ ድረስ ከሸዋ ሮቢት እስከ ቃሊቲ ድረስ ለአመታት በኢትዮጵያን እስር ቤቶች ያሳለፈው ይህ ደፋር ወጣት ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር በመሆን የመጀመሪያውን ክፍል መረጃውን ይፋ አድርጓል፡፡ አለማየሁ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጸው ከሆነ ተስፋዬ ከኤርትራው የደህንነት መስርያቤት ጋር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት የተለዋወጣቸው ምስጢራዊ ሰነዶችና ኦዲዮቪዧል መረጃዎች በአለማየሁ አስደማሚ ጥበብ ኮፒ ተደርገው ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለያዩ ክፍሎችም ለህዝብ ይቀርባሉ፡፡ በአለማየሁ መረጃ አቅራቢነት በዳኛ ወልደሚካኤል ተከሽኖ የቀረበው የመጀመሪያው የጽሁፉ ክፍል ከተለያዩ መረጃዎች ጋር እነሆ፡፡

Wednesday, October 2, 2013

Ethiopia challenging Norwegian aid politics



Ethiopian authorities are tightening the grip. Will the lack of respect for human rights tip the scale for Norwegian aid? (Photo: Joe Athialy/flickr.com)
Ethiopia has been a constant source of headache for Norwegian aid politics for the last few years, due to the authorities’ decreasing respect for human rights and political opponents. Ethiopian authorities have also earned a reputation for exerting strong control over aid money, using aid to keep political control. In addition, Norwegian-Ethiopian relations took a severe blow in 1998 when the war between Ethiopia and Eritrea caused Norwegian authorities to temporarily stop signing new agreements with Ethiopia. The relationship reached a freezing point after Norway in 2000 decided to shift the focus from bilateral agreements to stability, peace and reconciliation in the region.  
So why have not Norwegian authorities put an end to the troublesome relationship?

የጋምቤላን መሬት የተቀራመተው የህንዱ ካራቱሪ የንግድ ባንክን 62 ሚሊዮን ብር ዕዳን መክፈል ተስኖታል(zehabesha)

§ ኩባንያው የሠራተኞች ግብር፣ ጡረታ እንዲሁም
የክልሉን የመሬት ግብር አልከፈለም
§ ከቀረጥ ነጻ ያስገባቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና በመሸጥ እየተከሰሰ ነው
§ ከተረከበው 300 ሺ ሔክታር ያለማው 800 ሔክታር ብቻ ነው
በፋኑኤል ክንፉ

መሠረቱን በጋምቤላ ክልል ያደረገው የህንድ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኀ/የተ/የግ/ማህበር በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ሥራ ማከናወን አለመቻሉን እንዲሁም የባንክ ብድርና የግብር ግዴታዎቹን እየተወጣ አለመሆኑ ተገለፀ።
አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት ስለጉዳዩ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳስረዱት “ካራቱሪ ከባንኩ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2011 ወደ 62 ሚሊየን ብር ብድር መውሰድን አስታውሰው ነገር ግን መክፈል በሚገባው ጊዜ ሊከፍል አለመቻሉን፣ ብድሩንም ለማስታመም የተደረጉ ተጨማሪ ጥረቶች ባለመሳካታቸው ጉዳዩ ወደህግ ክፍል መመራቱን አስታውቀዋል። ባንኩ በአሁኑ ወቅት ይህ ብድር የተበላሸ ወይንም መመለስ የማይችል ነው በሚል ጉዳዩን ይዞት ለማስመለስ ወደ ሕጋዊ እርምጃ መግባቱን” ተናግረዋል።
በተያያዘም በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ከአራት ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል 300ሺ ሄክታር መሬት ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ተዋውሎ የገባው የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ ባለው ደካማ ማኔጅመንት ምክንያት ሥራውን ማከናወን ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

አባይ Vs ስብሃት ኔትዎርክ – (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

ዛሬም (እንደወትሮው) አንድ ቀሽም አስተያየት ልስጥ!
በህወሓት ዉስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ እያየን ነው። ስብሃት ነጋ የሚዘውረው ቡድን አንሰራርቶ የፖለቲካ የበላይነቱ የሚቆጣጠርበት ዕድል ሊኖር ይችላል (መላምት ነው፣ ከውዲሁ በዚህ ጉዳይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም)። የስብሃት ነጋ ኔትዎርክ ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የትግራይ ህዝብ ጠፍሮ ሲገዛና ሲያሰቃይ የነበረ ነው።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በሆነ ዉስጣዊ አለመግባብት ምክንያት የስብሃት ኔትዎርክ እየተመናመነ መጣ። አቶ አባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት ከሆነ በኋላ ኔትዎርኩ በሌሎች ተተካ። ይባስ ብሎ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ አቶ አባይ ወልዱ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነ። ከዚህ ግዜ ወዲህ ስለ አባይ ወልዱ ባህሪ መጥፎነትና የፖለቲካ ብቃት ማነስ በሰፊው ይወራ ጀመር።
እኔ የሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያህል የአባይ ወልዱ የተሟላ መረጃ የለኝም። እንደሌሎቹም በሓሳብ ክርክር ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም። (መለስ፣ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይ ጸሃየ፣ አርከበ፣ ቴድሮስ ሓጎስ፣ ፀጋይ በርሀ … ብዙዎቹ በደንብ አቃቸዋለሁ)። አባይ ወልዱ ግን በደንብ አላውቀውም። አንድ ግዜ ብቻ በሆነ አጋጣሚ ተገናኝተን ብዙ አውርተን ነበር (አብርሃ ደስታ መሆኔን ሳያውቅ ማለት ነው)። ያኔ እንዳየሁት ትህተኛ (humble) ይመስላል (በአንድ ግዜ የሰው ባህሪ ለመገምገም ቢከብድም)።
ስለዚህ ስለ የአባይ ወልዱ ፖለቲካዊ ብቃትና የግል ባህሪ ጥሩነት ወይ መጥፎነት መመስከር አልችልም። ቁልፍ የሚባል የህወሓት ስልጣን ለባለቤቱ መስጠቱ ግን እንደማንኛውም ሰው ገርሞኛል። ይህ እንዳለ ሁኖ ስለ አባይ ወልዱ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አባይ በህወሓት ካድሬዎች አይወደድም። አባይ የአምባገነንነት ባህሪ እንዳለውና የፖለቲካ ብቃት እንደሚያንሰው ለህዝቡ እንዲደርስ ተደርጓል። ማነው ስለ አባይ መጥፎነት የሚያወራ ቢባል መልሱ የህወሓት ካድሬዎች መሆናቸው ግልፅ ነው።
ለምን? አባይ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከመሆኑ በፊት ቁልፍ የህወሓት ኔትዎርክ ተቆጣጥረው የነበሩ ካድሬዎች የስብሃት ነጋ ታማኞችና ዘመዶች ነበሩ። ትግራይ ሙሉ ተቆጣጥረውት ነበር። አባይ ወልዱ የነሱ ዘመድ አይደለም። አባይ ስልጣኑ ከጨበጠ በኋላ የስብሃት ታማኝ ኔትዎርከኞች ስጋት አደረባቸው። ስጋታቸውም የህወሓት ኔትዎርከኞች ቀስ በቀስ ይቀየራሉ፤ ቁልፍ የሆኑ የስልጣን እርከኞችም ከስብሃት ታማኞች ወደ አክሱም ተወላጆች ይሸጋገራሉ የሚል ነበር።

የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ ነዉ የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) .

የአዜብ መስፍን የመያዝ እድል እየሰፋ መቷል:: የሙስና ንሰሃ አባቷ እና ባልደረባዋ ተይዟል:: በከፍተኛ ደረጃ በሙስና በመዘፈቅ ያለአግባብ ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ለቁጥር የማይገመት ሃብት አፍርተዋል የተባሉት ሃያሁለት አከባቢ የሚገኘው የኮሜት ሕንጻ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብረስላሴ ሃይለማርያም (አለቃ ገብረስላሴ) በቀጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በባለስልጣናት ዙሪያ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል:: የካፒታል ሆተል ባለቤት የሆነው ልጃቸውም እንዲሁ ሁኔታዎቹ እየተጣሩ ሲሆን የአለቃ ገብረስላሴ የሙስና መዝገቦች ከገብረዋህድ ጋር የተቆራኙ እና ከዚህም ጋር በተያያዘ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ይውላሉ ተብሎ ይጠበቃል:: የሙስና ንሰሃ አባት የሚባሉት እና በአቋራጭ የከበሩት በማናለብጭነት እና በትዕቢት በመንግስት ባለስልጣናት የሚመኩት አለቃ ገብረስላሴ ባለፉት አራት ወራት ከተያዙት እና የአዜብ መስፍን የሙስና አጋሮች ከሚባሉት መላኩ ፋንታ;ገብረዋህድ ወ/ጊ;ነጋ ገ/እግዜር;ስማቸው ከበደ ከተማ ከበደ እና ሌሎች የሙስና ባላባቶች ጋር እንደተያዙ ወዲያውኑ የቃሊቲን ቂሊንጦ ጎራ ተቀላቅለዋል:: እስካሁን ድረስ በፍርድ ቤት የቀረበባቸው የክስ ዝርዝር ባይታወቅም በመጪው የጥቅምት 14 እና 18 2013 ክሱ የሚሰማ መሆኑ ታውቋል::ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት አለቃ ገብረስላሴ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቃሊቲ መውረዳቸው አጠያያቂ ነው ሲሉ ተደምጥጠዋል::ሆኖም እንደመርማሪዎቹ ምንጮች ከሆነ የተከሰሱት በገብረዋህድ መዝገብ ጋር በአንድነት እንደሆነ ታውቋል:: ፋይሉ አከባቢ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በተከለከለው ከፍራንኮ ቫሉታ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ሲሚንቶ አስገብተዋል የተለያዩ እቃዎችን ቀረጥ ሳይከፍሉ አስገብተዋል በጉቦ እና በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ወዘት የሙስና ተግባራት ከባለስልጣናት ጋር ተመሳጥረዋል በሚለው ፋይል የተካተቱ ሲሆን በዚህ ፋይል ደሞ የአዜብ መስፍን የሙስና አጋሮች ገብረዋህድ እና ሚስቱ ሃይማኖት እንዲሁም የሰየ አብርሃ ወንድም ምህረተአብ ይገኙበታል:: — 

Tuesday, October 1, 2013

በአንድ የማይረባ አምድ ምክንያት facebook ጋደኞቼን አጣሗቸዉ

እንዲህ ሆነ አንድ ከወያኔ ወገን የሆነ ስዉ ethiopianre view ላይ ሁላችንም እንደምናደረገዉ የበኩሉን  የተሰማዉን  የተቃዉሞ አምድ ይፅፋል፤ ይህ ደግሞ መብቱ ነዉ፡፡  የአምዱ ርእስ› ማን ይሁን እውነተኛ፡ ኢሳት ወይስ ሪፖርተር?  ዝርርሩ ድግሞ  በቅረብ አንድነት በጠራዉ ተቀዉሞ ሰልፍ ላይ በሚደረግ ቅስቀሳ ላይ Dr. ነጋሶ ጊዳዳ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዜና ከኢሳትም እንዲሁም ከሌሎች social medias ሰምተናል፡፡ ችግሩ የተፈጠረዉ እዚጋ ነዉ፡፡ የወያኔ ወይም የመንግስት ደጋፊ የሆነዉ ሰዉ ኢሳትን እና ሪፖርተርን እያነፃፀረ ኢሳትን እየኮነነ የፅፋል፡፡ 
  ይፅፍና  ከላይ በጠቀስኩት ዌብ ሳይት ላይ ይለቃል፤ ያንኑ አምድ ደግሞ ለfaceebook friends ላላዩት ወይም አክሰሱ ለሌላቸዉ ፖስት አደረኩት፤ ይህን በማድረጌ  የፃፍኩትም እኔ ስለመሰልቸዉ ከየትኛዉ ጎራ ነህ የሚል ዉረጂብኝ  በዉስጥ መሰመሬ ለይ ጎረፈልኝ፡፡  አንድ ያልገባኝ ነገር ሠዉ አመለካከቱን  መግለፅ አይችልም እንዴ?  እኛ ወያኔን ስንተች ትክክል እነሱ በተቃራኒዉ  ሲሆን ሌላ እንዴት ነዉ ነገሩ? የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት እያለን  የፌስቡክ ጋደኛ መሆን አይቻልም እንዴ? ስለዚህ Please I don’t want to lose you.  I invite you to start our new facebook friendship again. 

ማን ይሁን እውነተኛ፡ ኢሳት ወይስ ሪፖርተር? (ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል)

ኢሳትም አለ፥ 
                          Breaking News Sep 25, 2013

ESAT-Salsaywoyane
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳም አሉ (ሪፖርተር)፥
salsaywoyane
ዝርዝሩን ከሪፖርተር ጋዜጣ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ … 
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው! ነው የሚባለው እርስዎስ ምን ይላሉ? ማን ይሁን እውነተኛ፡ ኢሳት ወይስ ሪፖርተር? ከምንም በላይ የገረመኝ ግን ኢሳት ሰበር ዜና ሲል ያልተጣራ ዘገባ ማቅረቡ ሳይሆን ጣቢያው (ኢሳት) ለመዋሸት ካለው ችኩልነትና ፍጥነት የተነሳ የፈጸማቸው የሥርዓተ ነጥብና የፊደል ግድፈት ነው። ሥርዓተ ነጥብና የፊደል ግድፈት የሚፈጽም ሁሉ ውሸታም ነው እያልኩ እንዳልሆነ አንባቢ ይረዳኛል የሚል እምነት አለኝ። አልፎ አልፎም ቢሆን የሥርዓተ ነጥብና የፊደል ግድፈት የማይፈጽም ማንም የለም። ታድያ አንድ ራሱን እንደ ተቋም የሚጠራ ድርጅት እንዲህ ዓይነቱ ተደጋጋሚ ጉልህ ስህተቶችን ሲፈጽም ግን ነገሩ አሳሳቢ ከመሆኑ አልፎ ተቋሙ ምን ያህል የሞያ ዝቅጠት አዘቅት ውስጥ መነከሩን የሚያሳይ፤ ተአማኝነት የሌለውና እምነት የማይጣልበት ዘርዛራ ወንፊት መሆኑ ጭምር አስረግጦ የሚናገር ነው።  መቼ ይህ ብቻ ሳይታሰሩ “ታሰሩ” ብሎ ዜና የሰራባቸው ግለሰብ አለመታሰራቸውን ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው እያወቀ ኢሳት ለፈጸመው ውንብድና ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳ አልደፈረም።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Oct 1, 2013

መሬት የማን ነው? አንድ

መስፍን ወልደ ማርያም
መስከረም 2005
አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ደም ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው።
የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች ደም እየፈሰሰ መሬቱ ላይ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁሉ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዲቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤
ይህ በአጥንትና በደም የታጠረ መሬት የማን ነው? በመሬቱ ላይ የባለቤትነት መብትን ለማስከበር ከውጭ ኃይሎች ጋር የተጋደሉት ጥንታውያን ነፍጠኞች ቅድሚያን የሚያገኙ ይመስለኛል፤ እነዚህ ጥንታውያን ነፍጠኞች ብቻቸውን አልነበሩም፤ ለምግብ የሚሆናቸውን ሁሉ የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፤ ለልብስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚፈትሉና የሚሸምኑ ባለሙያዎች ነበሩ፤ ልጆቻቸውን የሚንከባከቡና የሚያሳድጉም ለዘማቹ ምግብ የሚያቀብሉ እናቶች ነበሩ፤ በአጠቃላይ የሕዝቡን መንፈሳዊ ጤንነት ለመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኖችና በመስጊዶች የሚጸልዩ ሰዎች ነበሩ፤ ሰላምን የሚያስከብሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች ነበሩ፤ … አንድ ማኅበረሰብ ለተለያዩ የመደጋገፍ ሥራዎች የሚያስፈልጉት የሰዎች ዓይነት ሁሉ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ አጥሩን ለመገንባት አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ ስለዚህ መሬቱ የእነዚህ ሰዎች ሁሉ ነው።
ታሪካችንን በተግባር በኩል ስንመረምረው ግን መሬቱን እኩል እንዳልተካፈሉት እናያለን፤ ዛሬ ነፍጠኛ የሚባሉት መሣሪያ የታጠቁት ሰዎች ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው ሰፋፊ መሬት የመያዝ ዝንባሌ ነበራቸው፤ ነገር ግን ለማረስ የነበራቸው የሰው ጉልበትና የጥንድ በሬ ቁጥር የተወሰነ በመሆኑ ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር ብቻ ለሚፈልገው ገበሬ በቂ መሬት ይደርሰው ነበር፤ ሰፋፊ መሬት የያዙት ጉልበት አጥሮአቸው ሲቸገሩና ትናንሽ ማሳ ያለው ገበሬ ሰብሉ ቀንሶበት ሲቸገር በመጋዞ በማረስ ይረዳዱ ነበር (ገበሬዎችና ከብት አርቢዎችም ላሚቱ ስትወልድ ሴት ከሆነች ለከብት አርቢው፣ የከብት አርቢው ላም ወንድ ስትወልድ ለገበሬው እየተሰጣጡ ይረዳዱ ነበር፤) ሰፋፊ መሬት ያዙትም በጉልበት እጥረት ምክንያት፣ ትናንሽ ማሳ የያዙትም በትንሽነታቸው ምክንያት ከአስፈላጊው በላይ ስለማያመርቱ ትርፍ ምርት ቢኖርም በጣም ትንሽ ነበር፤ ከላይ እሰከታች ያለው ሰው ሁሉ የሚተዳደረው በመሬት ስለነበረ በጣም ጥቂት ለሆኑ ሰዎች (ቀጥቃጮች፣ አንጣሪዎች፣ ሸክላ ሠሪዎች፣ ሸማኔዎች … ወዘተ.) ለጉልበት ዋጋ ከሚከፈለውና ለአስተዳዳሪዎች ከሚከፈለው ግብር በቀር አብዛኛው ምርት ለቤት ፍጆታ ነበር።
እዚህ ላይ በመሬት ጉዳይ ላይ ለመታረም ያስቸገሩ ሁለት ስሕተቶችን ሳላመለክት ለማለፍ አልፈልግም፤ ብዙ ጊዜ እንዲታረሙ ብጥርም ፈረንጆች በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ በሙጫ አጣብቀውት ሊፋቅ አልቻለም፤ አንደኛ ገባር ማለት …read more

“ ያላወቂ ሳሚ …….. ይለቀልቃል”

ከጽዮን አምባዬ (ጀርመን)የዚህ ጽሁፍ ዓላማ አቶ መስፍን አብርሃ “መርዓዊና መንታ መንገዳቸው” በሚል ርዕስ የጻፈውና በኢትዮ.ሚድያ ላስነበበን ጽሁፍ በበኩሌ የማውቀውን ለማለት ነው። በቅድሚያ አሁን ካሉት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ለጥቂቶቹ ታናሽ ወንድም ለብዙዎቹ ወንድምና ታላቅ ወንድም የሆኑትን በምዕራብ አውሮፓ እንደ ሐዲስ ሐዋርያ የሚቆጠሩትን ካህንና ምሑር፤ ቄስ የሚለውን ማዕረግ እንኳን ነፍጎ መርዓዊ ብሎ መዘርጠጥ “አሳዳጊ የበደለው” ያሰኛል። ከዚህ አልፎ ጽሁፉም በዕውእነት ዙሪያ የሚያውጠነጥን አለመሆኑን ከአርስቱ ጀምሮ መረዳት ይቻላል። “መርዓዊና መንትያ መንገዶቻቸው” ልብ በሉ፤ ይህ መንታ መንገድ ከተፈጠረ 22 ዓመት አልፎታል። ነገሩን ግልጽ ለማድረግ ያህል፤ ቤተ ክርስቲያኗ በሁለት ሲኖዶሶችና በሁለት ፓትርያርኮች ከተከፈለች በኋላ መሆኑ ነው። ከዚህ ሌላ እኔም እንደ አቶ መስፍን እንዳለልዘረጥጥ ጥንቃቄ በማድረግ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ ከ30 ዓመት በኋላ የኋላ ማርሽ አስገብተው መንትያ መንገድ ላይ ይቆማሉ ብሎ ማሰብ ለጤነኛ አእምሮ አይሆንም። ከዚህም ሌላ በፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ራሳቸው በመሰረቱት ሀገረ ስብከት ሊቀ ካህናት ሁነው የተሾሙትን፧ አሁንም በኃላፊነት ላይ ያሉትን አባት “የዛሬው የጽሑፌ ቅኝት በቀድሞው የጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን “ኃላፊ” እና የኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ፤ በጀርመን የኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ብቻ ስለሆኑት ቀሲስ ዶክተር መርዓዊ ተበጀ አመራር ላይ ያጠነጥናል።“ ስትል፤ ይህ መቸም ከዚያው ከግብር አባተህ ከ……የተማርከው ቅጥፈትና ውሸት ካልሆነ በስተቀር እኔ እስከማውቀው ድረስ አሁንም ያው በኃላፊነታቸው ላይ እንዳሉ ነው። ጉደዩ ምንም ምሰጢርነት ስለማይኖረው፤ ማስረጃው አስፈላጊ ነውና ሲቀርብ እኔም እቀበለዋለሁ። አቶ መስፍን “በእርግጥ ግለሰቡ በጀርመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሥራች መሆናቸውን ማንም አይክድም።” ማለትህን እኔም እጋራዋለሁ። በልጃቸው አፍ “ግለሰብ” ተብሎ ሲነገር ግን መረን መልቀቅ ነው።